
እንኳን ለ43ኛው የካራማራ የድል በዓል አደረሠን!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ለካራማራ ጀግኖች መታሰቢያ አበባ በድላችን ሀውልት ሲያስቀምጥ

ስለማሳወቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አዲስአበባ
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትአዲስአበባጉዳዮ:-የምርጫ ቅስቀሳ የመክፈቻ ስነስርዓት ዝግጅትን ስለማሳወቅ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ዘመቻ የካቲት 8/2013ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ /ባልደራስ/ አማራ ብሔራዊ ንቀናቄ/አብን/ ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዋ አንድነት ፓርቲ/አብአፓ/ ከየካቲት 14-16/2013ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የምርጫ ቅስቀሳ የመክፈቻ ስነስርዓት አዘጋጅቷል ስለሆነም […]
የሀዘን መግለጫ
በኢዜማ ፓርቲ አባል በአቶ ግርማ ሞገስ ለገሰ ላይ በቢሾፊቱ/ደብረ ዘይት ከተማ የተደረገውን የግድያ ወንጀል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እጅጉን እንደሚያወግዘው እየገለፀ ለሟች ቤተሰብ እና ለባልደርቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ብሄራዊ መግባባት ሽብር ባልፈጸመ ሰላማዊ ታጋይ ላይ የሽብር ክስ በመመስረት ህጉን የፖለቲካ ተገዥ በማድረግ አይገኝም!!!
“እውነት ከአንባገነኖች ክንድ ትበረታለች”! እናት አገራችን ውዲቷ ኢትዮጵያ ከአያት ቅድም አያቶች አጥንት ፍላጭ ተማግራ፣ አፈሯ በደማቸው ተለዉሶ ተቦክቶና ተጋግሮ ለሺዎች ዘመን የቆመች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ ነገዶች ባህል ከባህል፣ሃይማኖት ከሃይማኖት ነገድ ከነገድ ተስበጣጥሮ ያቆማት የውህድ ማንነት ተምሳሌት ሀገር ናት፡፡ ይህም በልጆቿ ተጋድሎ ለዘመናት ከውጭ ወራሪ ሀይል ተጠብቃ በመቆየት የጥቁር ህዝብ ፈርጥ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ሆኖም በልጆቿ […]
የማንነት ፖለቲካ ምንነትና አደጋዎቹ ባህላዊ ማንነትን ፖለቲከኛ ስናደርግ ያመረትናቸው ችግሮች(ገለታው ዘለቀ )
የማንነት ፖለቲካ ይህን ስያሜውን ያገኘውና በሚታይ መልክ ብቅ ያለው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር። በዚሁ ወቅት የሴቶች ንቅናቄ፣ የጥቁሮች ንቅናቄ፣ የአካለ ስንኩላን ንቅናቄዎች፣ የብሔር ንቅናቄ በስፋት የታዩበት ጊዜ ነበር። የማንነት ፖለቲካ ወደ አካዳሚክ ዲስኩር የገባውም በዚሁ በቅርቡ ነበር።የማንነት ፖለቲካ ስንልም በእነዚህ ማንነቶች ላይ የሚሰራ የፖለቲካ ቤት ማለታችን ነው። ወደዚህ ፖለቲካ የሚገቡ ሃይሎች ደግሞ የፕራይሞርዳያሊዝም […]
ስር የሰደደው የዐቢይ የተቋም አተካከልና ክትትል ችግር (ገለታው ዘለቀ)
ከሁለት አመታት በፊት በሃገራችን የፖለቲካ ለውጥ የሸተተን መስሎን ስለ ሽግግር ብዙ አልን፤ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ለውጡ መጣሁ መጣሁ ሲል በፍጥነት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አለብን የሚል ድምጽ አሰሙ:: ይህ ድምጽ ግን በጣም የጥቂቶች ነበር:: አብላጫው ሰው ዶ/ር አብይ የሚመሩት መንግሥት የሽግግሩን ሥራ ይስራው የሚል ነበር:: ለለውጡ በጣም የሳሱ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የዶ/ር አብይን መንግሥት በርታ፣ ጎበዝ፣ […]
ፍርድ ቤቱ ሆይ! (አስካለ ደምሌ፤ ከቃሊቲ ወህኒ ቤት (የፖለቲካ እስረኛ))
በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከስሸ ያለ አንዳች ጥፋት ቃሊቲ ወህኒ ቤት እገኛለሁ።More/ተጨማሪ…
ፈሪሃ እስክንድር (ጌጥዬ ያለው)
የዚህ መጣጥፍ ርዕስ እስክንድር ነጋ ከአሳሪዎቹ እንደሚበልጥ ለማሳየት የተሰየመ እንጂ ስጋ ለባሹን ሰው ከፈጣሪ ለማስተካከል እንዳልሆነ ይታወቅ፡፡ More/ተጨማሪ…