የሃሳብ ልዩነት የችግር መፍትሔ ወይስ ምንጭ?
በህይወቴ ይችን ስንክሳር ዓለም ተቀላቅየ እዚህ ደረጃ እስከ ደረስኩበት ጊዜ ድረስ ለቅጥር አሻራ ለመነሳት ካልሆነ በቀር አንድም ቀን የፖሊስ ጣብያን ረግጨ አላውቅም፡፡ ለአሻራ በሄድኩበት ቀንም መለዮ ለባሽ አይቼ የተንቀጠቀጥኩበት ጊዜ አልነበረም፡፡ አሁን ግን የተለየ ነው፡፡ በፌደራል መንግሥት ወኽኒ ቤቶች ስር ውስጥ የሚገኘው ቃሊቲ ወኽኒ ቤት ስደርስና ወደ ውስጥ ገብቼ ልፈተሸ ስዘጋጅ የነበረኝ የፍርሃት ስሜት በቃላት […]