ለእውነተኛ ፍትህ የሚጨነቅን ሰው በፍትህ ዕጦት ማስጨነቅ የግፍ መጨረሻ ነው !!
የባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ባልተገኙበት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ተገቢነት የለውም።አቃቤ ሕግ ምስክሮችን በግልፅ ችሎት አቅርቤ ምስክር ማሰማት አልችል በማለት ሰበብ መሪዎቻችን የተፋጠነ ፍትህ እንዳያገኙ እየሰራ መሆኑን ከጅምሩ ፓርቲያችን ይረዳል።ጠ/ፍ/ቤቱ የቀጠሮ ቀን ከመወሰኑ አስቀድሞ የመከራከሪያ ጭብጡን ግልባጭ ጠበቆቻችን በተደጋጋሚ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምላሽ ሳያገኙ […]
እንኳን ለ43ኛው የካራማራ የድል በዓል አደረሠን!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ለካራማራ ጀግኖች መታሰቢያ አበባ በድላችን ሀውልት ሲያስቀምጥ
ስለማሳወቅ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አዲስአበባ
ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤትአዲስአበባጉዳዮ:-የምርጫ ቅስቀሳ የመክፈቻ ስነስርዓት ዝግጅትን ስለማሳወቅ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የምረጡኝ ቅስቀሳና የምርጫ ዘመቻ የካቲት 8/2013ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ /ባልደራስ/ አማራ ብሔራዊ ንቀናቄ/አብን/ ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዋ አንድነት ፓርቲ/አብአፓ/ ከየካቲት 14-16/2013ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የምርጫ ቅስቀሳ የመክፈቻ ስነስርዓት አዘጋጅቷል ስለሆነም […]
የሀዘን መግለጫ
በኢዜማ ፓርቲ አባል በአቶ ግርማ ሞገስ ለገሰ ላይ በቢሾፊቱ/ደብረ ዘይት ከተማ የተደረገውን የግድያ ወንጀል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እጅጉን እንደሚያወግዘው እየገለፀ ለሟች ቤተሰብ እና ለባልደርቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ውስጠ ወይራው ያለመለወጥ ‘ለውጥ’ (በቃሉ ሰውመሆን (የሕግ ባለሙያ)
አቢቹ ሰብሮ የወጣው ወያኔ የጣለውን እቁላል ነው፤ በጥቅሉ ከ 1960 ዓ.ም ወዲህ እስካለንበት በተከሰተው እንዘጭ እቦጭ ውስጥ ኢትዮጵዊነትን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረገ እራስ በል እና እራስበሉን አስቀጣይ የሆነ ሽግግራዊ ክሽፈት አጋጥሞናል፤ አንደኛው የክሽፈት አንጓ የንጉሳዊ ስርአቱን አንጸባራቂ ውርሶች አዘምኖ ማሸጋገር ሲገባ ለአውዳሚ አቢዮት መዳረጋችን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የኢሕአዴግን አራሙቻ ስርአት የሚነቅል አብዮታዊ የስርአት ለውጥ ማዋለድ ሲገባን […]
አኬልዳማዋ ኢትዮጵያ(ውቤ ደነቀው መኮንን)
ትሕነግ/ኢሕአዴግ ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሊበላትና ሊበታትናት ሲሠራ ቆይቷል:: ሲያስገነጥል ውድ ታጋይ ልጆቿንም ቁም ስቅል ሲያሳይ የነበረው ይህ ቡድን በቆራጥ፣ ግንባራቸውንና ደረታቸውን ለሀገር ሲሉ ራሳቸውን ለጥይት የሰጡት ጀግና ከሕዝብ አብራክ የተገኙ የእማ ኢትዮጵያ ውድ ፍሬዎች በከፈሉት የህይዎትና የአካል መስዋዕትነት የተገረሰሰው ነውረኛና ሆዳም ቡድንን ተከላከልኩ ብሎ አዲስ ለመጣውና ኢትዮጵያን ወደ ሰላምና ዴሞክራሲ ይወስዳል ተብሎ […]
የማንነት ፖለቲካ ምንነትና አደጋዎቹ ባህላዊ ማንነትን ፖለቲከኛ ስናደርግ ያመረትናቸው ችግሮች(ገለታው ዘለቀ )
የማንነት ፖለቲካ ይህን ስያሜውን ያገኘውና በሚታይ መልክ ብቅ ያለው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር። በዚሁ ወቅት የሴቶች ንቅናቄ፣ የጥቁሮች ንቅናቄ፣ የአካለ ስንኩላን ንቅናቄዎች፣ የብሔር ንቅናቄ በስፋት የታዩበት ጊዜ ነበር። የማንነት ፖለቲካ ወደ አካዳሚክ ዲስኩር የገባውም በዚሁ በቅርቡ ነበር።የማንነት ፖለቲካ ስንልም በእነዚህ ማንነቶች ላይ የሚሰራ የፖለቲካ ቤት ማለታችን ነው። ወደዚህ ፖለቲካ የሚገቡ ሃይሎች ደግሞ የፕራይሞርዳያሊዝም […]
ስር የሰደደው የዐቢይ የተቋም አተካከልና ክትትል ችግር (ገለታው ዘለቀ)
ከሁለት አመታት በፊት በሃገራችን የፖለቲካ ለውጥ የሸተተን መስሎን ስለ ሽግግር ብዙ አልን፤ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ለውጡ መጣሁ መጣሁ ሲል በፍጥነት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አለብን የሚል ድምጽ አሰሙ:: ይህ ድምጽ ግን በጣም የጥቂቶች ነበር:: አብላጫው ሰው ዶ/ር አብይ የሚመሩት መንግሥት የሽግግሩን ሥራ ይስራው የሚል ነበር:: ለለውጡ በጣም የሳሱ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የዶ/ር አብይን መንግሥት በርታ፣ ጎበዝ፣ […]