ባልደራስ ከክ/ከተማ አመራሮች እና ከንቁ ተሳታፊዎች ለተውጣጡ አባላቱ የሰጠውን ስልጠና አጠናቀቀ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በልደታ ክፍለከተማ የክልል እጩ ተመራጭ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ መኩሪያ ከሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናቶች በድርጅታችን ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ለሆኑ ከሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ለተወጣጡ አባሎቻችን በስድስት ተከፍለው ለሁለት ሁለት ቀናቶች በአጠቃላይ ለ12 ተከታታይ ቀናቶች የማህበራዊ ድህረ ገፅ አጠቃቀምን በማስመልከት ስልጠና ሰጥተዋል።
በስልጠናውም-: የፓርቲያችን አባሎች ማህበራዊ ድህረ ገፅን ሲጠቀሙ ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ እውነትን መነሻ እና መድረሻው አድርገው መጠቀም እንደሚገባቸውና የተሳሳቱ ዜናዎች (fake news) በቀላሉ እንዴት መለየት እንደሚቻል፣ ማህበራዊ ድህረ ገፆችን የፖለቲካ ንቃት ለመፍጠር እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ በማህበራዊ ድህረ ገፅ መተላለፍ ስለሚገባቸው እና ስለማይገባቸው የመልዕክት አይነቶች በስፋት ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ስልጠናው በፓርቲው ፅ/ቤት አስተባባሪነት እና በማህበራዊ ጉዳዮች ባለሙያ በሆኑት አቶ ኤርሚያስ መኩሪያ ስልጠና ሰጪነት ሲከናወን ቆይቷል። ስልጠናው አባላትን ለማብቃት ከሚሰሩ ስራዎች አንዱ ነው።
ድል ለዲሞክራሲ!!!