ባልደራስ ጋዜጣ(BALDERAS NEWSPAPER)
“ገበታ ለሀገር” – ከዶሮና ዓሳ ወግ አንጻር(ከማለፊያ ደርሰህ)
ዶሮና ዓሳ የቀረበ ገበታ አይተው ወግ ይጀምራሉ:: በገበታው ላይ የቀረበው ምግብ የዕንቁላል ጥብስና ዓሳ ነው:: ዶሮው “ይህ ገበታ ጣፋጭ ሆኖ ትላልቅ መሳፍንትና መኳንንት ተደስተው እንዲመገቡ ለማድረግ የእኔ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው:: ምክንያቱም እንቁላሉን የጣለችው ሚስቴ ዶሮ ነች፤ እንቁላሉ የሁለታችንም ዶሮዎች አበርክቶ ነው” ብሎ ተኩራራ::ዓሳውም ተደንቆ “እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳሉ” ብሎ ተረተና “ሰማህ ዶሮ፣ […]
ውስጠ ወይራው ያለመለወጥ ‘ለውጥ’ (በቃሉ ሰውመሆን (የሕግ ባለሙያ)
አቢቹ ሰብሮ የወጣው ወያኔ የጣለውን እቁላል ነው፤ በጥቅሉ ከ 1960 ዓ.ም ወዲህ እስካለንበት በተከሰተው እንዘጭ እቦጭ ውስጥ ኢትዮጵዊነትን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረገ እራስ በል እና እራስበሉን አስቀጣይ የሆነ ሽግግራዊ ክሽፈት አጋጥሞናል፤ አንደኛው የክሽፈት አንጓ የንጉሳዊ ስርአቱን አንጸባራቂ ውርሶች አዘምኖ ማሸጋገር ሲገባ ለአውዳሚ አቢዮት መዳረጋችን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የኢሕአዴግን አራሙቻ ስርአት የሚነቅል አብዮታዊ የስርአት ለውጥ ማዋለድ ሲገባን […]
አኬልዳማዋ ኢትዮጵያ(ውቤ ደነቀው መኮንን)
ትሕነግ/ኢሕአዴግ ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሊበላትና ሊበታትናት ሲሠራ ቆይቷል:: ሲያስገነጥል ውድ ታጋይ ልጆቿንም ቁም ስቅል ሲያሳይ የነበረው ይህ ቡድን በቆራጥ፣ ግንባራቸውንና ደረታቸውን ለሀገር ሲሉ ራሳቸውን ለጥይት የሰጡት ጀግና ከሕዝብ አብራክ የተገኙ የእማ ኢትዮጵያ ውድ ፍሬዎች በከፈሉት የህይዎትና የአካል መስዋዕትነት የተገረሰሰው ነውረኛና ሆዳም ቡድንን ተከላከልኩ ብሎ አዲስ ለመጣውና ኢትዮጵያን ወደ ሰላምና ዴሞክራሲ ይወስዳል ተብሎ […]
የማንነት ፖለቲካ ምንነትና አደጋዎቹ ባህላዊ ማንነትን ፖለቲከኛ ስናደርግ ያመረትናቸው ችግሮች(ገለታው ዘለቀ )
የማንነት ፖለቲካ ይህን ስያሜውን ያገኘውና በሚታይ መልክ ብቅ ያለው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር። በዚሁ ወቅት የሴቶች ንቅናቄ፣ የጥቁሮች ንቅናቄ፣ የአካለ ስንኩላን ንቅናቄዎች፣ የብሔር ንቅናቄ በስፋት የታዩበት ጊዜ ነበር። የማንነት ፖለቲካ ወደ አካዳሚክ ዲስኩር የገባውም በዚሁ በቅርቡ ነበር።የማንነት ፖለቲካ ስንልም በእነዚህ ማንነቶች ላይ የሚሰራ የፖለቲካ ቤት ማለታችን ነው። ወደዚህ ፖለቲካ የሚገቡ ሃይሎች ደግሞ የፕራይሞርዳያሊዝም […]
ሙሉ መጽሔቱን ለማውረድ/ Download