ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
የሀዘን መግለጫ !
በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል ዕጩ በአቶ በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር የተደረገውን የግድያ ወንጀል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እጅጉን እንደሚያወግዘው እየገለፀ ለሟች ቤተሰብ እና ለባልደርቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ዘመቻ ይቁም!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በአፋር አርብቶ አደር ወገኖቻችን ላይ በተፈፀመው ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የአፋር ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን ይመኛል። ኦሕዴድ/ብልፅግና ኢትዮጵያን ከቻለ አፍርሶ በራሱ ቀለም እንደገና ለመሥራት ይህ ካዳገተውም እንደ ሐረሩ የራስ መኮንን ሀውልት አፈራርሶ ለመተው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እናምናለን። ቅርሶችን ጨምሮ ነባር የኢትዮጵያ መገለጫዎችን የማፍረስ እና አንዳዶችን በአዲስ የመተካት […]
ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!
ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!ከሁሉ አስቀድመን በአገራችን በኦሮምያ ክፍለ-ሃገር በተለያየ ወቅት በተደጋጋሚ በተፈጸመ ጥቃት ፤ በንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና ኦነግ ሸኔ በተባለ የዳቦ ስም የተሰጠው ገዳይ ቡድን አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ እውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገልጻል!የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡በንጹሃን […]
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በጽኑ እናወግዛለን !
ባለፉት ዓመታት በተለይ “ለውጥ” መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በዜጎች ላይ የሚፈፀመውን የዘር ፍጅት ወንጀል በአይነቱ እና በመጠኑ እየጨመረ መጥቷል ። ለዚህም ዋንኛው ምክንያት አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት እንደሆነ ብዙ አስረጂ የሚሻ ጉዳይ አይደለም ።በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ የተፈጸመው የዘር ፍጅት ወንጀል ከዚህ ቀደም በክልሉ ሲፈጸም ከነበረው አረመኔያዊ […]
We strongly condemn the genocide
It was learnt that genocidal acts were committed in West Wollega Zone Bone Kebele in March 31, 2021. Balderas for True Democracy strongly condemn the genocide which has been taken as a normal social practice during the Abiy’s Administration. We are deeply saddened by the news and may God give the victims eternal rest.The genocide […]
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ትብብርን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የሀገራችን ህዝብ ለዘመናት በተጫኑበት ኢዲሞክራሲያዊና አምባገነን አገዛዞች የተነሳ፣ በነጻነት እጦት፣በስቃይ እና በመከራ ኑሮውን እንዲገፋ ተደርጓል። ጭቆናን አስወግዶ የሚፈልገውን ፍትህ እና እኩልነት እውን ለማድረግ ከፍትኛ ዋጋ መክፈሉም እሙን ነው።ይሁንና የሃገራችን የለውጥ ፍላጎት እና እንቅስቃሴ ጅማሮው ሳይሳካ፣ ለቀጣዩ ዴሞክራሲያዊ ትግል ተስፋ ሊሆን የሚችል መሰረታዊ የትርክትና የመዋቅር ክለሳ እንኳ ሳይደረግ አምባገነንነትና ዘረኝነት የእጅ ለውጥ ብቻ እያደረጉ የሚፈራረቁባት ሆናለች። […]
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የምርጫ ቦርድ አሻጥር አስመልክቶ ከባልደራስ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !
1ኛ. ከሁሉ አስቀድመን፣ በአገራችን ምዕራብ ኦሮምያ ክልል፣ ወለጋ ውስጥ፣ በሆሮጉድሩ ወረዳ ውስጥ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ከ60 በላይ ንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ ይገልጻል፤ የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ፓርቲያችን በአማራ እና […]
መንግሥት በአማራ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ እንዲቆም እንጠይቃለን!
በኦሮሚያ፤ ሆሮጉድሩ ወለጋ አቤ ደንጎሮ አማራዎች ካለፈው ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ በነሲብ እየተገደሉ ነው። የሚገደሉትም በመንግሥታዊ የእዝ መዋቅር በታገዘ ታጣቂ ቡድን ነው። ከግድያ የተረፉት ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ሕፃናት እየታነቁ ወንዝ ውስጥ መወርወራቸውንም ከአካባቢው የወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። በጉጂ፤ አማሮ ተመሳሳይ ብሔር ተኮር ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው።በመሆኑም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) […]