ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና አቶ ካሳሁን ደስታ እስር ህገ ወጥ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ እንዲፈታቸው ባልደራስ አበክሮ ያሳስባል
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና የፓርቲው ንቁ አባልና ጉዳይ አስፈፃሚ አዲስ አበባ ውስጥ ትላንት ህዳር 03/2015 ዓ.ም. በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል፡፡ በቅድሚያ የታሠሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ሲሆኑ ለእሳቸው ስንቅ ለማቀበል አቶ ካሳሁን ደስታ በሄዱበት ወቅት እሳቸውንም ፖሊስ አስሮ አስቀርቷቸዋል። የአዲስ አበባ መሥተዳድር እና የኦህዴድ/ብልጽግና መር መንግሥት ቆሜለታለሁ ከሚለው […]
በኦሮሚያ ክልል በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፕሮግራማዊ ተልእኮ እየተመራ ያለው የአማራን ዘር የማጥፋት ኢ-ሰብዓዊና አፀያፊ ድርጊት ሊቆም ይገባል
ቀን 29/03/2015 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ የሚኖሩ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና በሸኔ ሽብርተኞች ጥምር ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሐን በግፍ መጨፍጨፋቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአማራ ተወላጆች በየጊዜው በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በአማራ ተወላጆች ላይ በተካሔደው ጭፍጨፋ ኦነግ ሸኔ የተባለው ሽብርተኛ ቡድን ግንባር ቀደም መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ ግን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ተሳታፊ እንደሆነ በገሃድ […]
የደራ አማራን የዘር ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
የሰላም ድርድሩን አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ።
በህወሓትና በኦህዴድ/ብልፅግና መሃል ያለው የስልጣን ሽኩቻ እንጅ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዳልሆነ ይታወቃል። በሶስተኛው ዙር ጦርነት ወቅት በኦህዴድ/ብልፅግና መንግሥት በኩል የህወሓትን የመዋጋት አቅም ሙሉ በሙሉ እንዲንኮታኮት ማድረግ መቻሉ በገሃድ ታይቷል። ይሁንና በሁለት ምክንያቶች ኦህዴድ/ብልጽግና በጦርነት ያገኘዉን ድል ያረጋገጠለትን የደቡብ አፍሪካ ስምምነት በናይሮቢ ስምምነት እየሻረዉ እንደሆነ የሰሞኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ኦህዴድ/ብልጽግና የህዉሃት ወታደራዊ/ፖለቲካዊ አደረጃጀት እንዳይከሰም የሚፈለገባቸዉ ምክንያቶች ሁለት […]