ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
” የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም። ድምፅ ተዘርፏል”
የስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለይ የአዲስ አባባ የቅድመ ምርጫ ሂደት እና የድህረ ምርጫ የነጻ፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ መሆኑን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል። “ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ዘርፈውታል። ይህም በመሆኑ በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለው” ብሏል ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የምርመራ ውጤት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ […]
በምርጫው ጉዳይ ላይ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛ አገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ በማሰባሰብ አጠናክሮ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ፣ በድምጽ አሰጣጡ እና ቆጠራው የነበሩ ችግሮችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ፓርቲያችን አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ […]
ኢትዮጵያ መቼ ይሆን ነፃ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የሚኖራት ?!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ፍትህ እንዲሰፍን ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ፣ አድሎአዊነትና ዘረኝነት እንዲወገድ፣ሕዝብ ከመፈናቀልና ከድህነት እንዲላቀቀቅ፣ አዲስ አበባ የራስ ገዝ አስተዳደር እንድትሆን እና ሌሎችም ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሰፍኑ የሚያስችል ሥርዓት ለማምጣት ጠንክሮ ሠርቷል፤እየሰራም ነው፡፡የሃገሪቱ መሪ ‹‹ከባልደራስ ጋር ግልጽ ጦርነት እንከፍታለን›› እያሉ በተናገሩበት ወቅት እንኳን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከመታገል ቁርጠኛ አቋሙ ወደ ኋላ አላለም፡፡ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ […]
የባልደራስ የምርጫ ዘመቻ ዝግጅት ማብቂያ ፕሮግራም ላይ የተደረገ ንግግር
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ባለፉት አራት ወራት የቅድመ ምርጫ እንቅስቃሴው በሃራዊ እና በአዲስ አበባ ነክ ጉዳዮች ፓርቲው የሚያራምደውን ፖሊሲዎች ለከተማው ሕዝብ በተለያዩ መድረኮች እና የቅስቀሳ ዜዴዎች ለማሳገንዘብ ጥረት ሲደርግ ቆይቷል፡፡ በሃገር አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለውን አመለካከት በሃገር አቀፍ ማኒፌስቶው አስፎሮ አሰራጭቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን ሕዝብ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ ቢመርጠው፣ ስር የሰደዱ የከተማይቱን […]
የሐዘን መግለጫ
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት የሰማነው፣ በጥልቅ የሐዘን ስሜት ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣የኢትዮጵያ፡ቁዋንቁዎችንና ፡ሥነጽሑፍ እንዲኹም ታሪክ አስመልክተው ፣አያሌ የጥናትና የምርምር መጻሕፍትን ያበረከቱ ብርቅ፡ኢትዮጵያዊ፡ምሁር፡ነበሩ።የቋንቋ ፣የሥነ ጽሑፍ፣የታሪክና የሥነመለኮት ሊቁ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ በተለያዩ አገራዊና አህጉራዊ የፖለቲካ እድገት አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ይሰጡዋቸው፡በነበሩቱ በሳል ሀሳቦቻቸው እና ትችቶቻቸው ይታወቁ፡ነበር።እኚህ ሀገራቸውን ወዳድ፣ ዓለም አቀፋዊ ምሁር […]
በአዲስ አበባ በ218 የምርጫ ጣቢያዎች የታዩ ተግዳሮቶች የዳሰሳ ጥናት ውጤት !
1. የጥናቱ መሰረታዊ ሀተታ (Statement of the Problem)እንደ “UDHR“(1948) ክፍል 3 አንቀፅ 21 ድንጋጌ መሠረት የመንግሥት ሥልጣን መሰረቱ የሕዝቡ ፈቃድ ይሆናል፤ይህ ፈቃድም በየተወሰነ ጊዜ በሚደረግ እውነተኛ ምርጫ አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን ምርጫም በምስጢራዊ የድምጽ አሰጣጥ ወይም መሰል ነፃ ሂደት ሁሉን አቀፍና እኩል አሳታፊ በሆነ መንገድ የሚካሄድ ይሆናል።በተመሳሳይ ሁኔታ “ICCPR“ (1966)አንቀጽ 25 ድንጋጌ መሰረት እያንዳንዱ ዜጋ በዘር፣ቀለም፣ፆታ፣ቋንቋ፣ሐይማኖት፣የፖለቲካ […]
ሀገርን የማዳን ጥሪ – የመጨረሻው መጀመሪያ
ከባልደራስ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተሰጠ ሀገርን የማዳን ጥሪ (Balderas Support in North America )ለብዙ ሺህ አመታት በአባቶቻችን መስዋዕትነት የቆየችው ሀገራችን ዐይናችን እያየ እጃችን ላይ ሳትፈርስ ሁላችንም በአንድ ላይ ልንቆም ይገባል!የተከበራችሁ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን የዛሬ ሦስት ዓመት በአገራችን የተካሄደው ለውጥ በልባችን ውስጥ ሰንቆት የነበረው ተስፋ ከህሊናችን በቀላሉ የሚጠፋ […]
የሀዘን መግለጫ
ባለፉት ሁለት ቀናት በሰሜን ሸዋ መንግስት-መር በሚመስል መንገድ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ ጥልቅ ሀዘን የተሰማው ሲሆን በተሰማን ጥልቅ ሀዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም እንደማይኖር ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በሞት ለተለዩን ወገኖቻችን ፈጣሪ እረፍትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን፤ ለተጎዱ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡