ታሪክ ምስክር ነው (ውቤ ደነቀው መኮንን)
ይላል የቀድሞ ሰው ጉድ ነው የፍንጅርቱ
እናቲቱን አንች ልጅዬውን አንቱ
ማድረጉ ሲገርመው ሌንጮን አማካሪ እስኬውን ታሳሪ
ብሎ እያጠየቀ የመሪ ተግባር ነው? ወይስ የመሰሪ?
እንግዲህ ኢትዮጵያ ጠንክረህም ታገል ከችግር ተማር
ባልደራስ መጣልህ እራሱነን ፈቶ ፍፁም ነፃወጥቶ ከህሊና እስር በፍፁም ተላቆ ከፍርሃት ቆፈን
መሪውን አድርጎ ታላቅ እስክንድር
ስንታዬው ይልሃል አሻግሮ ሲያማትር
ቀለቡን ሰንቆ ወንዝ የሚሻገር
በአስካል በፀዳሉ ተውቦ በሀገር
በትግል ጠንክሮ ምርጫን አሸንፎ ሊያፀና ሀገር
ይመስገን ይወደስ ከባደረቦቹ ታጋይ እስክንድር ታላቁ እስክንድር፡፡
በቦሌም በየካ ባልደራስ ለምልሟል
በአዲስ ከተማና በአራዳም አብቧል
በኮልፌ ነፋስ ስልክ በአቃቂም አሽቷል
በቂርቆስ ጉለሌ ልደታም አፍርቷል
መላው አዲስ አበቤ በሙሉ ኢትዮጵያ ከባልደራስ ጋራ ለድል ተዘጋጅቷል
ባልደራስ ሲያሸንፍ ባልደራስ ድል ሲያደርግ ሁሉም ሰላም ይሆናል፡፡
ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላለ የሞተልሺ ሳይሆን የገደለሽ በላ
እንዳይሆን ተረቱ ከአሁን በኋላ አሳልፎ የማይሰጥ ድሉንም ለሌላ
ይፈጠራል ዜጋ ይፈጠራል ወጣት በእውቀት የተሞላ ወኔው የማይላላ
የጀግና ልጅ ጀግና የእሳት ልጅ እረመጥ ይሉሀል፣ ይሉሻል ይሄ ነው
የቴዎድሮስ ልጁ የሚኒሊክ ወንድም የበላይ ዘለቀ የንጉስ ሚካኤል የአብዲሳ አጋም ነው
ለሀገሩ ሞቶ ወገኑን ያኖረው
(በካድራ ወንዝ) ሞቶ ኢትዮጵያን ያኖረው
በፍጹም አይሞትም በጭራሽ አልሞተም ምን ጊዜም ህያው ነው
ጊዜ የሚያወጣው ጊዜ የሚገልጠው ታሪክ ምስክር ነው፡፡
ታሪክ ምስክር ነው (ውቤ ደነቀው መኮንን)