ሀጅ ደስታዎት ደስታየ ነው !
ሀጂ ሁሴን ይባላሉ። በንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ይኖራሉ። የምርጫ ጣቢያ 17 ተሰራ የተባለውን ወንጀል ለማጣራት ላፍቶ ጎራ ባልንበት አጋጣሚ ነበረ ያገኘኋቸው።
አጋጣሚ ስራ ውለው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በግል ተሽከርካሪያቸው ወደቤት በመመለስ ላይ ነበሩ። የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ ላይ ሲደርሱ በቅፅበት መኪናቸውን ዳር አስይዘው በማቆም ወደ ጣቢያው ቀረቡ።(የምርጫ ካርድ ለመውሰድ ነበር)
እኛ ደግሞ ማጣራት የፈለግነው ጉዳይ ጨረሰን ከትንሸየዋ ቆርቆሮ ቤት በመወጣት ላይ ነበርን። በዚህ ሁነት ከሀጅ ሁሴን ጋር ፊት ለፊት ተገጣጠምን። ሲያዮኝ ፊታችው በሃሴት ተሞላ። ትከሻየን እየዳባሱ “ወላሂ ወላሂ አንተን ነበር መንግስት ማደረግ!” አሉኝ። (ላለመዋሸት እንዲህ ሲሉኝ የኔም ልብ ፍስሃ ሞላው) ለምን ብየ ሳልጠይቅ ቀጠሉና “ያለችን አንድ አገር ነው፤ተለዋጭ ቦታ የለንም፤እኔ ኢትዮጵያን በጣም ነው የምወዳት ወላሂ ኢትዮጵያን ለማደን ሂወቴን ሁሉ እሰጣለሁ። ዛሬም የምርጫ ካርድ አውጥቼ አምባገነኖችን መልስ ለመስጠት ነው የመጣሁት። በዚህ አጋጣሚ ባንተ ዕድሜ ያለ ወጣት ለዛውም ያልተከፋፋለችውን ኢትዮጵያ አንገቱ ላይ አስሮ በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። ወላሂ።” ዕጅግ ደስታ ተሰማኝ። ኢትዮጵያን አንገቴ ላይ አስሬ ለሌላው ደስታ በመሆኔ።
ሀጅ ደስታዎት ደስታየ ነው።እኔም አገሬ ኢትዮጵያን አምርሬ ነው የምወዳት። አመሰግናለሁ ሀጅ እ/ር ይስጥልኝ። ለምን ፎቶ አንነሳም ብየ ጠየኳቸው፤በፈገግታ መለሱልኝ። ከደሬቴ ላይ ኢትዮጵያን አንስተው ደጋግመው እየሳሙ ይህን ፎቶ ተነሳን። በተጨማሪ የጥንካሬ፣የተስፋና የአንድነት ምልክት የሆነውን ቀኝ እጃችንን ከፍ አድርገን ደግመን ተነሳን። ስንጨርስ ተቃቀፍን።አመስግኘ ተሰናበትኳቸው። “ማሽ አላህ! ማሽ አላህ! ደና ሁን” አሉኝ።
ለመላው የዕስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ
“ዒድ ሙባረክ” !!!!
ወግደረስ ጤናው
ግንቦት 2013