“One of the penalties for refusing to participate in politics is that you end up being governed by your inferiors.” — Plato
“በፖለቲካ ውስጥ ባለመሳተፍኽ ከሚመጡብህ ቅጣቶች መካከል አንዱ ከአንተ አስተሳሰብ የበታች በሆኑ ሰዎች መመራት ነው።”፦ ፕላቶ
ከላይ ያለው የፕላቶ ጥቅስ በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በጥሩ ሁኔታ ይገልፃል። አቅሙ እያላቸው በፖለቲካዊ ሂደቶች ላለመሳተፍ የሚመርጡ ግለሰቦች በበዙ ቁጥር፤ ብቃት የሌላቸው ሰዎች ሥልጣን ላይ ሊቀመጡ ወይም ሊገዙ እንደሚችሉ ነው።
የፖለቲካ ተሳትፎ እንደ ዜግነት ግዴታ መሆኑ ተጠብቆ፤ ለቦታው የሚመጥኑ ግለሰቦችን ወደ ስልጣን እንዲመጡ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል። ነገር ግን እነዚህ ብቃት ያላቸው ግለሰቦች ከፖለቲካ ተሳትፎ በታቀቡ ቁጥር ብቃት የሌላቸው ሰዎች ክፍተቱን የመሙላት ዕድል ያገኛሉ። ይህ ደግሞ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ የስቃይ ምንጭ የሆኑትን፦ የመልካም አስተዳደር ብልሹነት፣ ሰብዓዊ መብቶች ያለመከበር፣ የፍትሕ መጓደል፣ የአገልግሎቶች አቅርቦት በብቃት ያለመከናወን፣ እንዲሁም ሙስናና ምግባረ ብልሹ አሠራርን በሀገር ላይ ያነግሳሉ።
ቁጥራቸው የማይናቅ ሰዎች ብዙ ጊዜ በኩራት “በፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ አልገባም ወይም አልሳተፍም” ፣ “ኮረንቲና ፓለቲካ በሩቅ!” ሲሉ ይሰማሉ። ይህ ማለት በሌላ አገላለፅ፦ ስለኑሮ ደረጃዬ፣ ስለጤንነቴ፣ ስለሥራዬ፣ ስለመብቴ፣ ስለነጻነቴ፣ ስለወደፊት ሕይወቴ፣ስለልጆቼ የወደፊት ዕጣ ፈንታ… በተመለከተ የመወሰን ፍላጎት የለኝም እንደ ማለት ነው። እነዚህ ምሳሌያዊ አነጋገሮች በማህበረሰቡ ውስጥ የአስተሳሰብና የስነልቦና ችግር ፈጥረዋል። ህዝብን በፍርሃት፣ በጭንቀት፣ በሀዘን፣ በተስፋ መቁረጥ፣ በህመም፣ በመከራ ፣ በኢፍትሃዊነት የተበተበ እንዲሆን አድርገውታል።
በአሁኑ ሰአት ብዙዎች እንደሚስማሙበት፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ ለመታገል የሚሸማቀቅባት ሀገር ሆናለች። በዚህም ምክንያት ቤተመንግስቱን የተቆጣጠሩ ኃይላት ተቃዋሚዋሚቻቸውን በዱላ፣ መካሪዎቻቸዉን በልምጭ፣ ሕዝባቸዉን በጦርነት፣ በረሐብ፣ በድሕነት የሚያገርፉባት ሐገር ሆናለች። ለዚህ መፍትሄ የሚሆነው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ በአካል፣ በሃሳብ፣ በፋይናንስ.. ወዘተ በመሳተፍ የከሸፈውን የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሊታገሉ ይገባል። ፕላቶ እንዳለዉ፣ በአቅም ባነሱ ሰዎች ወደተሳሳተ አቅጣጫ ላለመመራት አማራጩ ‘የፖለቲካ ተሳፎ’ ነውና።
The above quote from Plato perfectly explains the current political situation in Ethiopia. Plato’s words essentially mean that if you remain indifferent to public affairs or politics, you risk becoming a victim to those with ill intentions. Good people, in general, do not seek to control others. On the other hand, corrupt individuals require control over others to avoid accountability for their wrongdoings.
Many people often say, with pride, “I am not interested in politics.” They might as well be saying, “I am not interested in my standard of living, my health, my job, my rights, my freedoms, my future, or any future.” If we intend to maintain any control over our country and lives as Ethiopians, we must take an interest in politics.
Traditionally, there is a saying, “ኮራንቲ ና ፓለቲካ በሩቁ,” which discourages involvement in politics and has created harmful beliefs in society, leading to untold negative consequences—fear, anxiety, sadness, hopelessness, pain, suffering, and injustices of all kinds.
Although the political landscape in Ethiopia is notoriously restrictive, posing significant challenges for opposition parties to operate freely and pursue peaceful struggle, it is high time for patriotic Ethiopians to become actively involved in opposition politics by contributing ideas, finances, and support. Such involvement is essential to challenge the failed political, social, and economic policies of the Prosperity Party.
Written by: Ameha Hailemariam from the North America Support Group.