በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሴት ዕጩዎች ብቻ የተመራ የምርጫ ቅስቀሳ !
” አዲስ አበባን ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋታለን !”
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
” አዲስ አበባን ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋታለን !”
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በወሰነው መሰረት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ በመጭው ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት እንዲቀርቡ ለማድረግ ሥራዎችን መጀመሩን አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ቀርዋል።
ቦርዱ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እንደሚፈፅምም ተናግረዋል። የዕጩዎቹን ስም ዝርዝር እና በእነ ማን እንደሚተኩ ለቦርዱ ያቀረበው ባልደራስ ለእነ እስክንድር ነጋ የዕጩነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጠው መጠየቁን የፓርቲው የሕግና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሓላፊ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ቀሪ ሥራዎችን አጠናቆ ሰነዱን ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በፍርድ ቤቱ ፊት እንዲያቀርብም ቀጠሮ ተይዟል።
እንደ ቦርዱ ማብራሪያ ዕጩዎቹን ለማተካካት በተደረገው እንቅስቃሴ ታትሞ የነበረ 1.3 ሚሊዮን ወረቀት ተወግዷል። በዚህም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጭ ተደርጓል።
ፍርድ ቤቱ ለሰኔ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል
በቃሊቲ ወህኒ ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) መሪዎች ማለትም እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። በባልደራስ የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪዎችም ችሎቱን ታድመዋል። የኅሊና እስረኞችን በመወከል አቶ ስንታየሁ ቸኮል ችሎቱን ለታደሙ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪዎች በችሎቱ ፊት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ እስክንድር ነጋ ባለፈው ግንቦት 17 የዋለውን ችሎት በአርምሞ ተከታትለው የወጡ ሲሆን ዛሬም በእሳቸው መዝገብ ከተከሰሱ ሁሉም የኅሊና እስረኞች በተለየ በዝምታ ሲከታተሉ ውለዋል። በአንፃሩ ክርክሩን በንቃት ወረቀት ላይ ሲፅፉ አስተውለናል።
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ወደ እስር ፍርድ ቤት መልሶ በላከው መሰረት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ቢቀርቡ ዐቃቤ ሕግ ሊደርስባቸው ይችላል ባላቸው ስጋቶች ላይ ክርክር ተደርጓል። ዐቃቤ ሕግ ‘የስጋት ትንተና’ ያለው፤ ነገር ግን በይዘቱ ጥቅል የሆነ ጉዳይ ከዚህ ችሎት አስቀድሞ ለዳኞች በፅህፈት ቤት በኩል በፅሁፍ ቀርቧል። በተመሳሳይ የኅሊና እስረኞች ጠበቆችም ስጋቱን ፉርሽ ያደረገ መከራከሪያ በፅሁፍ አቅርበዋል። ዛሬ የዋለው ችሎት የፅሁፍ ክርክሮችን ማብራራት ላይ ያተኮረ ሲሆን ከወትሮው ረዘም ያለ ጊዜም ወስዷል።
ዐቃቤ ሕግ የምስክሮችና ጠቋሚዎች ጥበቃ አዋጅ 699/2003ን በመጥቀስ አምስት ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባ ማንነታቸው ሳይታወቅ እንዲመሰክሩለት እንዲሁም 16ቱ በዝግ ችሎት እንዲመሰክሩለት ጠይቋል። ከዚህ በፊት በቅድመ ምርመራ ወቅት ምስክሮች በዝግ ችሎት ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ አንድ ምስክር ላይ በሽጉጥ የግድያ ሙከራ መደረጉን ገልጿል።
ይህ የግድያ ሙከራ እንዴት፣ የት እና በማን እንደተፈፀመ ከተሰየሙት ሶስት ዳኞች መካከል የቀኝ ዳኛዋ ላነሱት ጥያቄ ዐቃቤ ሕግ ምላሽ አልሰጠም። በተመሳሳይ አስቴር ስዩም “የግድያ ሙከራው እንዴት ተደረገ? ማን ነው ያደረገው? የባልደራስ አመራር፣ አባል፣ ደጋፊ ነው ወይ?” ሲሉ ጠይቀዋል። ዐቃቤ ሕግ ይህንን ጉዳይ በተደጋጋሚ ባደረጋቸው ንግግሮች መልስ ሳይሰጥ አልፎታል። በመጨረሻም ሰብሳቢ ዳኛው ለዚህ ጥያቄ መልስ እንዲሰጡ በችሎቱ የተሰየሙ ሦስት ዐቃቤ ሕጎችን ቢጠይቁም ምላሽ አልተሰጣቸውም።
“ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ምስክሮች ከዚህ በፊት ዛቻ እና የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሆነ ይታወቃሉ ማለት ነው። የሚታወቁ ከሆነ ከመጋረጃ ጀርባ እና በዝግ ችሎት መቅረባቸው እንዴት ከጥቃት ሊያድናቸው ይችላል? በማለት ችሎቱ ጠይቋል። “ተከሳሾች ታዋቂዎችና ብዙ ደጋፊዎች ያሏቸው በመሆኑ ደጋፊዎቻቸው ጉዳት ያደርሱባቸዋል” ከማለት በዘለለ ዐቃቤ ሕግ አላብራራም። ከመጋረጃ ጀርባ እና የዝግ ችሎት አስፈላጊነትን በተመለከተም ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቆ “ምስክሮቻችን በግልፅ ችሎት የመመስከር ፍላጎት የላቸውም” ብሏል። በግልፅ ችሎት የሚመሰክርለት እማኝ አለማግኘቱንም ጠቁሟል።
በተያያዘ “ምስክሮች በግልፅ ችሎት ከቀረቡ ስማቸውን እና ምስላቸውን በፌስቡክና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማራጮች በማሰራጨች ማህበራዊ መገለል ያደርሱባቸዋል” ሲል ስጋቱን ጠቁሟል። ጠበቆች በበኩላቸው “አንድ ሰው ከሚኖርበት ማህበረሰብ እሴት ሲያፈነግጥ ማህበረሰቡ ራሱ ማህበራዊ ቅጣት ይቀጣል። ይህ በማህበረሰብ እሴት እንጂ በሕግ የሚታይ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል።
ዐቃቤ ሕግ እነ እስክንድር ነጋ እና ጠበቆቻቸው በሌሉበት ችሎቱ በምስጢር የምስክሮቹን ቃል እንዲቀበልለትም ጠይቋል። ይህንን የሰሙት ወይዘሮ አስቴር ስዩም “እንዲህማ ከሆነ ዐቃቤ ሕግ ራሱ አይፈርድም ወይ፤ ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ማየት የለበትም ወይ?” በማለት ቢጠይቁም በቀጣዩ ችሎት ምላሽ እንደሚሰጣቸው ገልፀው ዳኞች አልፈውታል።
የምስክሮች ስጋት ያላቸውን ዐቃቤ ሕግ በዝርዝር አለማቅረቡን ያስረዱት ጠበቆች በንፅፅር የዩጎዝላቪያን ተሞክሮ አብራርተዋል። በዩጎዝላቪያ ተፈፀመ በተባለ ወንጀል ምስክሮች በስውር እንዲቀርቡ ተጠይቆ ስጋቶች በተጨበጫ መቅረብ ስላልቻሉ ጥያቄው ውድቅ መደረጉን አስረድተዋል። በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ዐቃቤ ሕግ እያቀረበው ያለው ጥያቄ ከዓለም ዓቀፍ የፍርድ ስርዓት ውጭ መሆኑንን ተናግረዋል።
ይህንን ያከራከረው ፍርድ ቤቱ ከመጭው ምርጫ በኋላ ለሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የምርጫ እንቅስቃሴው ካለፈ በኋላ በርካታ ታዳሚዎች ባሉበት ለመፍረድ እንደሚያመቻቸውም ሰብሳቢ ዳኛው ተናግረዋል። ከአንድ ወር በኋላ ቀጣዩ ችሎት በተደረገ ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የፍርድ ቤቶች ዓመታዊ ረፍት የሚደረግበትና ዝግ የሚሆኑበት ጊዜ እንደሚጀምር ይታወቃል።
በውሳኔው መሰረት ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽም ባልደራስ በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም፤ ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ውሳኔን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚቸገር እና ተፈጻሚ እንደማያደርግ በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል ።
ይህን ተከትሎ የባልደራስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ በማካሄድ ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለህግና ለፍትህ ተገዢ አለመሆኑን አጽኖት በመስጠት
የፍትሕ ሂደቱ ጠብቆ አፈፃፀም እንዲቀጥል በወሰነው መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአፈጻጸም መዝገብ ከፍቷል ።
ፍ/ቤቱ የባልደራስ አቤቱታ በመቀበል ፤ ምርጫ ቦርድ እንደ ፍርዱ ፈጽሞ እንዲቀርብ ለግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፊታችን ሰኔ 14 ሊካሄድ የታቀደው ምርጫ እንዲታገድ፤ ባልደራስ ባቀረበው አቤቱታ ላይ ምርጫ ቦርድ ምላሽ እንዲሰጥ በተመሳሳይ ቀን ቀጠሮ መሰጠቱን የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ገልጸዋል ።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ስለህግ የበላይነት እና የፍትህ አካላት ሚና በአማራጭ መፍትሔነት በምርጫ ማኒፌስቶ (መጋቢት፣ 2013 ዓም) በግልፅ እንዳስቀመጠው “በኢትዮጵያ የሚኖረው የፖለቲካ ሥረዓት የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ይሆናል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ ወይም መንግስታዊ አካል ለህግ የበላይነት ተገዢ ይሆናል፡፡ መንግስት የሚመራበት ህግ ግልፅ የሆነ፣ አስቀድሞ በአዋጅ የወጣና የግለሰቦችን መሰረታዊ ሰበዓዊ መብት የሚጠብቅና ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ ከህግ አግባብ ውጪ መብቱን፣ ነፃነቱን፣ ንብረቱን እና ጥቅሞች እንዳይነኩ የህግ ጥብቃና ዋስትና ያገኛል፡፡ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተደራሽነት ያላቸው የፍትህ አካላት በየደረጃው ይቋቋማሉ፡፡ በህዝብ ተሳትፎና ነፃ ምርጫ የሚፀድቀው ህገ መንግስት የሁሉም ህጎችና መንግስታዊ ውሳኔዎች የበላይ ሆኖ ያገለግላል፡፡”
እኛ ባልደራሶች የህግ የበላይነት የማይገረሰስበት እንዲሁም ፍትህ የሰፈነባትን ታላቅ የሠለጠነች አገር እንድትኖረን ዘውትር መትጋት ግዴታችን ነው!!!!
* * * * *
ኢንጂነር ዓለማየሁ ንጋቱ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ምርጫ ክልል 19 የባልደራስ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።
በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ እንደማይፈፅም በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል ።
ይህን ተከትሎ የባልደራስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።x