ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የፈራ ይመለስ”
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የፈራ ይመለስ” መፅሐፉ ላይ እስክንድር ነጋን እንዲህ ሲል ገልፆታል።
“እስክንድር ነጋ ለእኔ ከነ አሉላ አባ ነጋ፣ከእነ ዘረዓይ ደረስ፣ ከነ አብዲሳ አጋ ትይዩ የሚቆም የአገር ባለውለታ ጀግና ነው። “
”የያዝኩትን መሬት ኢትዮጵያዬን እንዳልለቅ የመንፈስ ብርታት የሆነኝም ይህ ሰው ነው።”
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የፈራ ይመለስ” መፅሐፉ ላይ እስክንድር ነጋን እንዲህ ሲል ገልፆታል።
“እስክንድር ነጋ ለእኔ ከነ አሉላ አባ ነጋ፣ከእነ ዘረዓይ ደረስ፣ ከነ አብዲሳ አጋ ትይዩ የሚቆም የአገር ባለውለታ ጀግና ነው። “
”የያዝኩትን መሬት ኢትዮጵያዬን እንዳልለቅ የመንፈስ ብርታት የሆነኝም ይህ ሰው ነው።”
የወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥት በ1960ዎቹ መጨረሻ አካባቢ በእስክንድር ነጋ ወላጆች ላይ የተለያዩ በደሎች በማድረሱ ጨቅላውን እስክንድርን ይዘው ወደአሜሪካ ተጓዙ፡፡ እስክንድር በአሜሪካ በቆየበት ወቅት ኢትዮጵያውያን የደርግን መንግሥት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች ሲያካሂዱ እሱም በዚያ በለጋ የተማሪነት ዘመኑ ሰላማዊ ትግሉን ተቀላቅሎ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
የደርግ መንግሥት ወድቆ ሕወሀት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ፣ እስክንድር ነጋ በ1985 ዓ.ም. ወደ ሀገርቤት ተመለሰ። ጊዜ ሳያጠፋም በጋዜጠኝነት ሞያ የካበተ ልምድ ከነበረው ከተፈራ አስማረ ጋር በመጣመር “ኢትዮጲስ” የተሰኘች ሳምንታዊ ጋዜጣን በማሳተም በወቅቱ ሀገሪቷን በመሣሪያ ኃይል ከተቆጣጠሩት ወያኔና ሻእቢያ ጋ የጦፈ የብዕር ጦርነት ገጠመ።
ከ1985 ዓ.ም. እስከ 1987 ዓ.ም. ባሉት ሁለት ዓመታት ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት በቆሙ ወደ 40 በሚደርሱ መጽሔቶች ላይ ምሁራዊ ጽሑፎች እንደ ውሃ ጅረት ሲፈሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ጽሑፎች የወያኔንና የሻብያን መሪዎች በብስጭት ጨርቅ ሲያስጥሉ፣ የአዲስ አበባን ነዋሪ የተቃጠለና የአረረ አንጀት ቅቤ አጠጥተዋል፡፡ የእነ እስክንድር “ኢትዮጲስ” ጋዜጣም እጅግ ተወዳጅ ከመሆኗ የተነሳ፣ የጋዜጣ መሸጫ ዋጋ ከአንድ ብር ያነሰ የነበረ ቢሆንም፣ በጋዜጣ አዟሪዎች እጅ፣ እስከ ሰባት ብር በሚደርስ ዋጋ ትሸጥ ነበር።
በዚያን ወቅት አብዛኛው ሕዝብ የኑሮ በጀቱ እስኪቃወስ ድረስ መጽሔትና ጋዜጦችን እንደ መደበኛ የምግብ አስቤዛው እየገዛ ስለሀገሩ ጉዳይ ያነብ ነበር፡፡ የሕዝብን ቀልብና አእምሮን ከማረኩና የወያኔን ካምፕ ካሸበሩ የኢትዮጲስ ጽሑፎች መካከል “የማትረባ ፍየል” በሚል ርእስ በካርቱን መልክ የወያኔውን መሪ ምስል ለጥፋ ያስነበበችው እትም ከእነ እስክንድር የብዕር ትሩፋቶች አንዷና የማትረሳ ሆና በብዙዎች ዘንድ ትታወሳለች።
ከ1987 ዓ.ም. በኋላ የብዕር ጦርነቱን መቋቋም ያቃተው ወያኔ የጋዜጣና መጽሔት አዘጋጆችን ማሳደድ እና ማሠር ጀመረ። ከ40 ይበልጡ የነበሩ የብዕር ምርት ይታፈስባቸው የነበሩ መጽሔቶችና ጋዜጦች በአጭር ጊዜ እየከሰሙ ሄዱ። የእነ እስክንድር ኢትዮጲስ ጋዜጣም እጣ ፈንታ ተመሳሳይ ሆኖ፣ እስክንድር ነጋና ተፈራ አስማረ ወደ ወህኒ ቤት ተወረወሩ። የነፃው ፕሬስ አከተመለት በሚባል ደረጃ ተሽመደመደ። በሁለት ዓመታት ውስጥ ጥሩ የማንበብ ልምድ ያዳበረው የአዲስ አባባ ህዝብም፣ ድብርት ውስጥ ገባ። የወያኔ የድንቁርና አስተሳሰብ ብቻውን ተንሰራፍቶ በከተማዋ ነገሠ። የየሳምንቱ የህዝብ ዋና መነጋገሪያ የነበሩት የጋዜጣ ጽሑፎች በእነእስክንድር የእስርቤት ውሎና አዳር እንዲሁም በፍርድ ቤት ችሎት ላይ በሚያሳዩት ጽናትና ጀግንነት ተተካ። የእነእስክንድር ከወያኔ ጋር ያደረጉት ድፍረትና ጀግንነት የተሞላበት የፍርድቤት ሙግትና ሰላማዊ የብዕር ጦርነት ለተተኪው ወጣት ጋዜጠኞች አርዓያነትን እያተረፈ መጣ።
የእነ እስክንድርን አርዓያነት የተከተሉ ብዙ የብዕር ታጋዮች የወያኔን ሀገር አፍራሽ አስተሳሰብ በጽሑፎቻቸው ሞግተዋል፡፡ በትግላቸውም ብዙ መከራና እንግልትን ተቀብለዋል። እንደዚያም ሆኖ እንደ እስክንድር ነጋ ወያኔ ኢሕአዴግን እየታሠረና እየተፈታ በጽናት ለረዥም ጊዜ ሲታገል የኖረ ብዕረኛ የለም።
የነፃው ፕሬስ በድጋሚ ባቆጠቆጠበትና ወያኔ ኢሕአዴግ አዲስ አበባ ላይ 23 ለባዶ በተሸነፈበት፤ በ1997ቱ ታሪካዊ ምርጫ ወቅት እስክንድር ነጋ ያሳትማቸው የነበሩት “ምኒልክ” እና “አስኳል” ጋዜጦች ኢትዮጵያ ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትራመድ ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር። “ምኒልክ” እና “አስኳል” ጋዜጦች በየሳምንቱ ከመቶ ሺ በላይ፣ ለሚደርስ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያቀርቧቸው የነበሩት ታሪካዊና ፖለቲካዊ የሆኑ በሳል መጣጥፎችና ትንተናዎች በንባብ ወዳዱ ኅብረተሰብ ልብ ውስጥ ዛሬም ታትመው ይኖራሉ።
ወያኔ እስክንድር ነጋን ከ1987 እስከ 2010 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ውስጥ ለአስር ዓመታት አስሮታል፡፡ ነገር ግን እውነተኛ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የመገንባትና የማየት ህልምና ራዕይ የሰነቀ ቆራጥ ስነልቦናውን መስበር አልቻለም።
እስክንድር ነጋ ለ27 ዓመት የታገለው ግፍ ሠሪው ወያኔ ከሥልጣን ከተወገደ 3 ዓመት አለፈው፤ ነገር ግን የለውጥ ኃይል ነኝ የሚለው ተረኛው መንግሥት እስክንድር ባልሠራው ወንጀል ካሠረው አንድ ዓመት አልፎታል። ኦሕዲድ መራሹ ኢሕአዲግ እስክንድር ነጋን በጠላትነት ያየባቸው ምክንያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል፣ ሀገራችን በታሪክ አይታ በማታውቀው ሁኔታ ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ የዘር ፍጅት ሲፈጸምባቸው ለእነሱ ድምጽ በመሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳወቁና አቤቱታ ማቅረቡ፣ የኦሕዴድ ብልጽግና መንግሥት በተረኛ ገዥነትና በማናለብኝነት ስሜት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቃቅር እርምጃዎች ሲወስድ መቃወሙ፣ ገዥው መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ህዝብን ከኖረበት መንደሩ ሲያፈናቀል፣ የንብረትና የመሬት ወረራን ሲፈጽምና፣ የቅርስ ማውደም ተግባራትን ሲያከናውን መከራከሩ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ፡፡
አንዲት ሀገር ብዙ መምህራን፣ ጸሓፍት፣ ሀኪሞች፣ ተመራማሪዎች፣ የጦር መኮንኖች ሌሎችም በተለያዩ ዘርፎች የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሊኖሯት ይችላሉ። ነገር ግን ጥሩ የሀገር መሪ ከሌላት ሀገሪቱ ከጉዳት ላይ መውደቋ የማይቀር ነው፡፡ የተለያዩ ሃገራት ታሪኮች እንደሚያሳዩት መሪዎች እራሳቸውን እያስቀደሙ ሀገርንና ሕዝብን ሲጎዱ ምሁራን ተስፋ እየቆረጡ፣ ሀገራቸውን እየጣሉ ይሰደዳሉ። ከ1966 ዓ.ም. በፊት ኢትዮጵያውያን በስደተኝነት አይታወቁም ነበር። ከ1966 ዓ.ም. በኋላ ግን በመሰደድ ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን በተለይም ምሁራን እጅግ በርካታ ሆኑ።
በሌላ በኩል ሀገራት፣ በቂ ምሁራን ባይኖሯቸውም ጥሩ መሪ ካገኙ ለሀገር የሚጠቅሙ ምሁራንን በየእውቀት ዘርፉ ለማፍራት ብዙ አይቸግራቸውም። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የቆየ ጥንታዊ ታሪክና ሥልጣኔ ያላቸው ሀገራት የወደቀውን ሁለንተናዊ ገጽታቸውን ለመመለስ በህዝብ ተቀባይነት ያለው ሩቅ አሳቢ ጠንካራ መሪ ማግኘት የግድ ይላቸዋል።
ባለፉት 60 ዓመታት በመልካም መሪ እጦት በተሰደዱበት ስለቀሩት ኢትዮጵያውያን ምሁራን በቁጭት መንፈስ እንዳነሳነው ሁሉ፣ ከስደት በፈቃዳቸው ተመልሰው ለሀገራቸው አርዓያነት ያለው ሥራን ስለሠሩ በጣት የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ገድል ሳንመሰክር ማለፍ አይገባንም። ከእነዚህ አንዱ ታሪኩን እየዘከርንለት ያለነው በአሜሪካን ሊገኝ የሚችለውን የተደላደለ ኑሮ በ20ዎቹ ዕድሜው ጥሎ ሀገሩን የሙጥኝ ያለውን እስክንድር ነጋ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለሀገር የጠቀሙ ታሪክ ሠሪ ሊቃውንትን እና ታላላቅ የሀገር መሪዎችን ስታፈራ የነበረች ጥንታዊት ሀገር ናት። ይህን ማድረግ የቻለችው ደግሞ ከትውልድ ወደትውልድ ሲሸጋገር በቆየው በመሪዎቻችን የአመራር ጥበብ መሆኑ አሌ አይባልም። የኢትዮጵያ መሪዎች አንድነቷን የጠበቀች ሀገር ያስረከቡን፣ እውነተኛ የሀገር ፍቅርና ፈሪሀ እግዚአብሔር የነበራቸው፣ ሀገራዊ ኃላፊነትን ለመሸከም ወደኋላ ያላሉ፣ ጥበበኛ የሆኑ፤ በራሳቸውና በሕዝባቸው የሚተማመኑ፣ ቆራጥና እውነተኛ መሪዎች ስለነበሩ ነው። ኢትዮጵያ እንደዚህ ዓይነት መሪዎችን ካየች 60 ዓመታት አለፏት። ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለሀገር ህልውናና እድገት የሚቆሙ መሪዎችን ማፍራት ተስኗት የቁልቁለት ጉዞ እየተጓዘች ትገኛለች። በዚህ የቁልቁለት ዘመን ለኢትዮጵያ ትንሳኤ መምጣት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ መሪዎችን ማግኘት መታደልን ይጠይቃል። በዚህ ረገድ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ከገባችበት መቀመቅ ሊያወጧት የሚችሉ ተስፋ የሚጣልባቸው ጥቂት ጥበበኛ የፖለቲካ መሪዎች እንዳሉ አይካድም። ላለፉት 30 ዓመታት በጽናት የታገለ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያልተለየው፣ ጀግና፣ ቆራጥ፣ ጽኑ፣ የዘመናችን የብእር አርበኛ፣ ኢትዮጵያዊ አንድነትና ሉዓላዊነት አጀንዳን አድርጎ የሚያራምድ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆነው እስክንድር ነጋ ለኢትዮጵያችን ተስፋዋ ነው።
በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ከገባችበት እጅግ አስቸጋሪ ከእርስ በርስ ጦርነትና ውስብስብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውጥንቅጥ ችግሮች ልትወጣ የምትችለው እንደ እስክንድር ነጋ ያሉ ለዲሞክራሲና ለፍትህ በጽናት የታገሉ መሪዎችን ቦታ ስትሰጥ ብቻ ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ የአዲስ አበባ ኗሪ፣ ሀገር ሁነኛ መሪ አጥታ፣ በእርስ በርስ ጦርነት በምትታመስበት በዚህ አስከፊ ወቅት፣ መሪውን እስክንድር ነጋን ችላ ሊል ከቶ አይገባም። ሕዝብ ለሀገሩ፣ ለባንዲራው፣ ለራሱና ለልጆቹ ህልውና ሲል መሪውን እስክንድር ነጋን ከእስር የማስፈታት ታሪካዊ ሓላፊነቱን ነገ ከነገወዲያ ሳይል ዛሬውኑ ሊወጣ ይገባል።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
( ነብዩ ውብሸት )
ነሃሴ 2013 ዓ.ም.
የባልደራስ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ አስካለ ደምሌ የታሰሩት፣ የሀጫሉን ግድያ ተከትሎ ብዙ ወንጀል እንዲሰራ ላደረጉት ሌሎች አካላት ማመጣጠኛ ነው። እነ እስክንድር ምንም ሳያደርጉ ታስረው ብዙ ወንጀል የሰሩ ግን አሁንም የሽግርር መንግስት በማቋቋም ላይ ናቸው። ዋናው ነገር እነ እስክንድር ምንም አይነት ወንጀል አልሰሩም ነው። ብዙ ንፁሃንን አስፈጅተው ለታሰሩት ማመጣጠኛ ተብለው የታሰሩት እነ እስክንድር ምንም ወንጀል ሳይሰሩ ነው የታሰሩትና ይፈቱ ስንለው ከከረምነው አሁን ተጨማሪ ምክንያቶች አሉን።
1) በዚህ ሀገር ምርጫ ያለው ጫና እየታወቀ፣ ከእስር ቤት ውጭ ያሉትና ቀስቅሰው ምርጫ ማድረግ የሚችሉትም ምርጫውን አንፈልግም ብለው፣ ኢትዮጵያን እየጎተቱ ላሉት የውጫ አካላት በየቀኑ መረጃ እያቀበሉ፣ አሁን ደግሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ቅብጥርጥስ ሲሉ በእስር ቤት ብዙ በደል እየደረሰባቸው ያሉት የባልደራስ አመራሮች ግን ምርጫውን እንሳተፋለን አሉ። ተሳተፉ። ከእነ ችግሩ ለተደረገ ምርጫ “ለመረጣችሁንም ላልመረጣችሁንም እናመሰግናለን” ነው ያሉት።
እስር ቤት ለብሶት የሚዳርግ ብዙ ነገር ስላለ ምርጫው አያስፈልግም አላሉም። ምርጫውን አላሸነፍንም ብለው አላንገረገሩም ። ችግር ስላልነበረበት አይደለም። ከራሳቸውም ከፓርቲያቸውም በላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ዙርያ ገባውን አይተው ነው። ይሄ የባልደራስ አመራሮች አካሄድ የሞራል የበላይነታቸውን፣ የአሳሪዎችን ባሕሪ በደንብ ያጋለጠ ነው። የብልፅግና ካድሬዎች “ኢትዮጵያ አሸንፋለች” ይላሉ።
ይህ አባባል እውነት ቢሆን ኖሮ የባልደራስ አመራሮች ነበር ማለት የነበረባቸው። ያለ አግባብ ታስረው፣ እስር ቤት ውስጥ ብዙ ጫና ችለው፣ መወዳደር አትችሉም ሲባሉ የፍርድ ሂደቱ ላይ እምነት አድርገው እስከመጨረሻው ተከራክረው፣ እስር ቤት ያሉ አካል እንደሚለው “ምርጫው አይጠቅምም” ሳይሉ ተሳትፈው፣ ከዛም ለመረጣቸውም ላልመረጣቸውም አመስግነዋል። ከዚህ በላይ ለዲሞክራሲ ሞዴል የት ይገኛል? ከዚህ በላይ ሀገር እንዲያሸንፍ የሚፈልግ ማን ነው? ከዚህ በላይ የራሱን በደል ችሎ ለሂደት የሚጨነቅ ማን አለ? ከእነዚህ እስረኞች የተሻለ በዚህ ወቅት ምስቅልቅል ውስጥ ለምትገኘው ኢትዮጵያ በአሳቢነት ማን ሊጠቀስ ይችላል?
2) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምርጫው ለተሳተፉ ፓርቲዎች እንደ ተሰትፏቸው ስልጣን እንደሚያጋሩ ተናግረዋል ። በሂደት የሚታይ ይሆናል። የሆነ ሆኖ በምርጫ ለተሳተፉት አጋራለሁ ያሉት ምንም ይሁን ምን በሂደቱ አምነው ስለተሳተፉ ነው። ባልደራስ በሂደቱ ተሳትፏል። እስር ላይ ያሉ አመራሮች ከእስር ቤት ውጭ ያሉትን ጓዶቻቸውን “እኛን እስር ቤት ጥላችሁ እንዴት ምርጫ ላይ ጊዜያችሁን ታጠፋላችሁ?” አላሉም። እነሱም ምንም ይሁን ብለው በሂደቱ ተሳትፈዋል። በምርጫው ከተሳተፉት ሁሉ የመጀመርያው እውቅናም ምስጋናም ሊሰጥ የሚገባው እስር ቤት ሆነው ለተሳተፉት ነበር።
ከእስር ቤት ውጭ ካሉት በባሰ በከፋ ሁኔታ ሆነው ነው ለምርጫ የቀረቡት። መንግስት መጋራቱ እስር ቤት ላሉት የባልደራስ አመራሮች ቅንጦት ነው። መጀመርያ ያለ አግባብ ከታጎሩበት መለቀቅ አለባቸው። ከዛ መንግስት ማጋራት የሚለው የሚታይ ይሆናል። በምርጫ የተሳተፉትን የባልደራስ አመራሮች እስር ቤት አጉሮ፣ ውጭ ሆኖ የተሳተፈውን አጋራለሁ ማለት ለጊዜያዊ ድጋፍ ማግኛ ነው የሚሆነው። የምር፣ የመርህ ከሆነ የባልደራስ አመራሮች ሊፈቱ ይገባል። ድሮም ተፈትተው ነበር ምርጫውን መሳተፍ የነበረባቸው።
3) መንግስት ከተሞችን በሮኬት ከደበደበው፣ ሰራዊቱን በተኛበት ካረደው፣ ሀገርን ለመበተን እየሰራ ካለው፣ በምክር ቤት ከተፈረጀውን ትህነግ ጋር እደራደራለሁ ብሏል። በአንፃሩ በምርጫ ሂደት አምነው የተሳተፉ፣ ሲሸነፉም “እናመሰግናለን” ያሉ የዲሞክራሲ ቀንዲሎችን በእስር አጉሯል። ይህ አካሄድ ክፉ ባህል ነው የሚያስለምደው። በቀል ካልሆነ በስተቀር እነዚህን ለሀገር አሳቢዎች እስር ቤት የሚያቆያቸው ጉዳይ የለም። ጥላቻ፣ መርህ አልባነት፣ መልካምነታቸውን መጥላት ከልሆነ በስተቀር እነዚህን ተምሳሌቶች እስር ቤት ማቆየት ለማንም አይጠቅምም።
ከእነ በርካታ ችግሩ የተካሄደን ምርጫ እስር ቤት ሆኖ የተሳተፈን አጉረህ፣ ጫካ ሆኖ ሀገር አፈርሳለሁ የሚል ጋር ሰላም እፈጥራለሁ ስትል ለሕዝብ እየነገርከው ያለኸው መሳርያ አንስቶ ለሚታገል ቦታ እንደምትሰጥ ነው። የመሳርያ አቅም ከሌለህ፣ የፈለገ ለሀገር ቀናኢ ብትሆን ጉዳዬ አይደለም ነው እያልከው ያለኸው። ሰራዊት እየከዳ፣ ሕዝብ እያረደ፣ ከውጭ ጠላት ጋር እየተሞዳሞደ ያለው ይመቸኛል፣ ከእሱ ጋር ነው የምግባባው ነው እያልክ ያለኸው። ምርጫውን ከእነ ችግሩ ችሎ የተሳተፈውን እንቀዋለሁ፣ እውቅና አልሰጠውም፣ አላበረታታም ነው እያልክ ያለኸው። ለዲሞክራሲ ከሚታትር ይልቅ ሽብርን መንገዱ ያደረገውን እመርጣለሁ እያልክ ነው። ይህ መንገድ አጥፊ ነው።
ለኢትዮጵያ የሚበጁት እስር ቤት ሆነው በምርጫ የተሳተፉት ፣ የመረጣቸውንም ያልመረጣቸውንም ያመሰገኑት፣ ለሂደቱ፣ ለሀገራቸው ሲሉ በሂደቱ የገጠመውን ሁሉ ከሀገር አይበልጥም ብለው ያለፉት ናቸው። እነ እስክንድር በማናጆነት ስለመታሰረቸው እነ ጃዋር ሳይቀር በፍርድ ቤት ተናግረዋል። ሕዝብ ቀርቶ ተቀናቃኞቻቸው፣ በብዙ አመለካከት የማይስማሟቸው፣ በእኛ ምክንያት ነው የታሰሩት ብለው ታዝበዋል። የባልደራስ አመራሮች በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል። መፈታተቸው ለሀገር ይጠቅማል። ብዙ ያስተምራል!
(ጌታቸው ሽፈራው)
እስክንድር ነጋ ፈንታ በ1960 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ተወለደ። አባቱ የአሜሪካው ሩትጋርት ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቤሩት አስተማሪ ነበሩ። በኋላም በአዲስ አበባ የግል የጤና ተቋም አቋቁመው በመንግሥት ንብረቶቻቸው እስከወረሰባቸውና ሥራቸውን እስካስቆመበት ጊዜ ድረስ ሀገራቸውን በብዙ አገልግለዋል።
እስክንድር እድሜው ለትምህርት ሲደርስ አዲስ አበባ በሚገኘው ሳንፎርድ ኢንግሊሽ ስኩል መማር ጀመረ። ትምህርት ቤቱ የተሻለ የትምህርት ጥራት እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎች አሉት፡፡ በሙያዊ ብቃታቸው የተመሰገኑ መምህራን ያሉት ሲሆን ተማሪዎችን ለማስተማር ት/ቤቱ የሚያስከፍለው ገንዘብም ከሌሎች ት/ቤቶች ሲነፃፀር ከፍተኛ የሚባል ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በዚሁ አጠናቆ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በሰሜን አሜሪካ ተምሯል።
ከዚያም ዋሽንግተን በሚገኘው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በመግባት ‘ኢኮኖሚክስ’ እና ፖለቲካል ሳይንስ አጥንቶ የማስተርስ ዲግሪውን ይዟል። በተማሪነት ጊዜውም የደርግን አምባገነናዊ ሥርዓት በመታገል አሳልፏል። የወታደራዊው አስተዳደር ደርግ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በከስክስ ጫማው ሲቀጠቅጥ ‹‹ለምን?›› በማለት ተቃውሟል። ቤተሰቦቹም ቢሆኑ ይህንኑ ሥርዓት አምርረው ተቃውመዋል። በአሜሪካ አደባባዮች በተደረጉ ደርግን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፎች እስክንድር ከነቤተሰቦቹ የፊት ተሰላፊ ነበር።
የሀገሩ ጉዳይ የሚያሳስበው እስክንድር ነጋ በ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ። ከጋዜጠኛ ተፈራ አስማረ ጋ በመሆን በ1985 ዓ.ም. ‘ኢትዮጲስ’ የተባለች ሳምንታዊ የፖለቲካ ጋዜጣ አቋቁመው የወያኔን ሀገር አፍራሽ አገዛዝ መቃወም ጀመሩ። ጋዜጣዋ በሕዝብ እጅግ ተወዳጅ ነበረች። የተጻፈላት መሸጫ ዋጋ 75 ሳንቲም ቢሆንም በሽሚያ እስከ 7 ብር ድረስ ትሸጥ ነበር። ሆኖም የመንግሥት አፈና የገጠማት ገና በሁለተኛዋ ዕትም ነበር። የታፈነችው ጋዜጣዋ ብቻ አይደለችም፤ እስክንድርም በተደጋጋሚ ይታሰርና ይፈታ ጀመር። አንደኛውን ጋዜጣ ሲዘጉት ሌላ እያቋቋመ በፅናት ለፕሬስ ነፃነት ታገለ።
ሐበሻ፣ ምኒልክ፣ አስኳል፣ ሳተናው እና ወንጭፍ የተባሉ ጋዜጦችን ማዘጋጀቱን ቀጠለ። እስክንድር በሥራ አስኪያጅነት በሚመራው ሰርካለም አሳታሚ ሥር ከሚታተሙ ጋዜጦቹ መካከል ምኒልክ፣ አስኳልና ሳተናው በተመሳሳይ ጊዜ ይታተሙ ነበር። ከሀበሻ በስተቀር ሌሎቹ ጋዜጦች በአማርኛ የሚታተሙ ሲሆን ሐበሻ ጋዜጣ በእንግሊዝኛ ነበር የምትታተመው። በይዘት ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነች፤ ልዩነቱ የቋንቋ ነው። ብዙ ጊዜ በእንግሊዝኛ የሚታተሙ ጋዜጦች በምሥራቅ አፍሪቃ ፖለቲካ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የማተኮር ዝንባሌ አላቸው። ሐበሻ ግን ሙሉ ትኩረቷ ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነበር።
ሀበሻ ጋዜጣ ተነባቢነቷ ሲጨምር በአማርኛም ለማሳተም እንቅስቃሴዎች ተጀመሩ። በአማርኛ ልትጀምር መሆኗን የሚያበስር ማስታወቂያ ‹‹ጎበዝ አምስት አመት ሞላን እኮ›› ከሚል ጉልህ ጽሑፍ ጋር በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በየመብራት እንጨቶች፣ በየአጥሩ እና በየግድግዳው ላይ ተለጠፈ። ማስታወቂያውን እስክንድር ከሌሎች ሰዎች ጋር ራሱ እየዞረ ነበር የለጠፈው። የሐበሻ ጋዜጣ ማስታወቂ በከፋፋይ ወያኔዎች ላይ ድንጋጤን ፈጠረ። በተለይ ‹‹ጎበዝ አምስት ዓመት ሞላን እኮ›› የሚለው አስከፋቸው። የሚችሉትን አደረጉና እስክንድርን አሠሩ። ጋዜጣዋም ሳትታተም በማስታወቂያ ቀረች።
ሁሉም ጋዜጦች የወያኔ/ኢሕአዴግን ሸፍጥ ፊት ለፊት የሚያወጡ ነበሩ። በዚህም ከዘጠኝ ጊዜ በላይ ታስሯል። እስክንድር ነጋ ለሃሳብ ነፃነት፣ ለሀገር ሰላምና አንድነት ሲል በቆራጥ ጋዜጠኝነቱ ለአስር ዓመታት ያህል በወያኔ ታስሯል። እርሱ ብቻ ሳይሆን ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልም አብራው ስትታሰር ኖራለች። በገዥው ፓርቲ የሚፈፀምባቸው ግፍ ከባልና ሚስቱም አልፎ ለልጃቸውም ወርዷል፤ ይኸውም ልጃቸው ናፍቆት እስክንድርም በቃሊቲ እስር ቤት መወለዱ ነው፡፡ እናቱ ሠርካለም ስላልተፈታች ናፍቆት ለአያቱ በመሰጠቱ ጡት የመጥባትን የህፃን ልጅ ወግ አላየም። በአንድ ግቢ ውስጥ ታስረው የሴትና የወንድ በሚል አጥር ተከልለው እስክንድር ሚስቱ በጥላቻ በሰከሩ አረመኔዎች ከለላ ሥር ሆና ስታምጥ ከጎኗ መገኘት አልቻለም። የቅርብ ሩቅ ሆኗል። ከዚህም በኋላም ለልጁ የቤት ውስጥ አባት መሆን አልቻለም፤ ከቤተሰቡ ይልቅ ትኩረቱን ለሀገሩ አድርጓልና።
እስክንድር በ2013 ዓ.ም. በቅርቡ በችሎት የተናገረውን ብናስታውሳችሁ፦ “በሕወሓት ጊዜ 10 ዓመት ታስሬያለሁ። በዚህኛው ሥርዓት ደግሞ ይኸው አንድ ዓመት ታሰርኩ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ልጄን አጥቸዋለሁ። ባለፈው ጊዜ ከእስር ቤት ወጥቼ ስሄድ ‹‹ማን ነህ?›› አለኝ። ዳኞች ቤተሰባዊ ጉዳያችንንም አስባችሁ ፍረዱ” አለ።
የፅናት ምልክቱ እስክንድር ነጋ በብዕሩ ወያኔን ሲፋለም ከአራት በላይ ታላላቅ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እስር ቤት ውስጥ ሆኖ አሸንፏል። ከእነዚህም መካከል በ2004 ዓ.ም. ፔን ባርባራ ጎልድስሚዝ የተባለ የጸሐፊያን ነፃነት ሽልማትን አግኝቷል። በ2006 ዓ.ም የወርቃማ ብዕር ሽልማት ተሰጥቶታል። በ2009 ዓ.ም. ከዓለም አቀፍ የፕሬስ ኢንስቲትዩት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና ሽልማትን በውድድር አሸንፏል። በ2010 ዓ.ም. ከኦክስፋም ኖቪ የብዕር ሽልማትን አግኝቷል።
እስክንድር ከወያኔ የእስር ካቴና እጁን ካላቀቀ በኋላም አዲሱን የኦሮሙማ የአብይ አሕመድ መንግሥት ለመቃወም ቀድሞ የተገኘ የማንቂያ ደወል ነው። ሀገሪቱ ወደ ኦሕዴድ አምባገነናዊ ተረኝነት መሸጋገሯን እንደ እርሱ ቀድሞ የተረዳ የለም።
በዚህ ሕዝባዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እምቢተኛ ባህሪው የተነሳ እስክንድር ነጋ ተመልሶ ወደ እስር ቤት ከገባ እነሆ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር ሆነው።
(ከጌጥዬ ያለው)
የሦስት ቀን የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ ጥሪ!
” ጳጉሜን ፤ ፍትሕ ለግፍ እስረኞች “
አገራችን ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት የገጠማት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን በእጅጉ ያሳስበዋል። በተለይ የወቅቱ የሃገራችን የፖለቲካና ወታደራዊ ሁኔታ አደገኛ ከመሆኑ አንጻር ጉዳዩን በጥንቃቄ በማየት ተገቢውን ውሳኔ መስጠት እንደሚያስፈልግ ከእነ መፍትሄ አሳብ ጭምር ባልዳራስ መግለጹ የሚታወቅ ነው።
አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፤ ህዝባዊ ኃይሎቹና የሌሎች ኢትዮጵውያን ኃይሎች የፖለቲካ ትብብር የራሳቸውን የአደረጃት ነፃነት በጠበቀ መልኩ፣ ሃገርን ለማዳን ሲባል ከመንግሥት ጋር ትግሉን በማቀናጀት መሥራቱ ሃገሪቱ ከገጠማት እጅግ ከባድ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ችግር በአሽናፊነት ለመውጣት የሚያስችል የፖለቲካ ስልት ጭምር እንደሆነ ባልዳራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከዚህ ቀደም በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፤ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ አስቴር ስዩም እና ወሪ/ት አስካለ ደምሌ ከ1 ዓመት በላይ ያለ ጥፋታቸው ፤ ለዲሞክራሲ ፣ ለፍትሕ እና ለእኩልነት በመወገናቸው እና የፖለቲካ አመለካከታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በግፍ ከታሰሩ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ አንዳች የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ አልቀረበባቸውም ። ዓመት ሙሉ ሲጓተት የከረመው የምስክሮች አሰማም ሂደት ከታችኛው ፍ/ቤት እስከ ሰበር ጠቅላይ ፍ/ቤት ተመሳሳይ ውሳኔ ቢሰጥም ምስክሮችም በግልጽ ችሎች መቅረብ እንዳማይችሉ መንግሥታዊው ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ በተደጋጋሚ ገልጿል ። በዚህ መሀል ንጹሃን ያለ ብይን ከአንድ ዓመት በላይ በግፍ እስር እንዲቆዩ ተደርገው እየተጉላሉ ይገኛሉ ።
በእስር ቤት ውስጥ ከሌሎች እስረኞች በተለየ በአቶ እስክንድር ነጋና በአቶ ስንታየሁ ቸኮል ላይ የወህኒ ቤቱ አያያዝ እጅግ በጣም የከፋ ሆኗል ። ይህንን አስከፊ የእስር ቤት አያያዝ አስመልክቶ ፍርድ ቤት እስረኞቹን አስመልክቶ
የቂሊንጦ ወህኒ ቤት አፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርግ ያስተላለፋቸው ትዕዛዞች አንዳቸውም ተግባራዊ አልተደረጉም። እነ እስክንድር ፖለቲካዊ መብቶቻቸውን በመንግሥት በኃይል ተነጥቀዋል ፣ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሰ ይገኛል።
ይህም በመሆኑ ፦ በሰላማዊ የነፃነት ታጋዮች ላይ እየደረሰ ያለው መንግስታዊ በደል ፣ የፍትሕ እጦት፣ የሰብዓዊ መብት ገፈፋ እና ያለ ጥፋታቸው መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ በአስቸኳይ ከግፍ እስር እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ሁሉን አቀፍና አሳታፊ የሆነ ” ጳጉሜን ፍትሕ ለግፍ እስረኞች ” በሚል መሪ ቃል የሦስት ቀን የበይነ መረብ ዘመቻ ይደረጋል፡፡ ዘመቻው ሰኞ ከጳጉሜ 1 እስከ ረብዕ ጳጉሜ 3/2013 ዓ.ም የሚደረግ ሲሆን መረጃዎች በመለዋወጥ ፣ ለኢትዮጵያውያን፣ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በማሳወቅ ላይ ያተኩራል፡፡
የበይነ መርብ ዘመቻው በፌስ ቡክ፣ በቲውተር ፣ በኢንስታግራም፣ በአገር ውስጥና በውጭ ባሉ ሬዲዬ፣ ቴሌቪዥን ፣ በምስል በድምፅ በፎቶና በካርቶን ስዕሎች፣ በቪዲዬዎች ይደገፋል። እነኚህ መልዕክት አስተላላፊ ዘዴዎች በመዓከል ደረጃ የሚዘጋጁ እንዳሉ ሆነው ፤ የዘመቻውን ዋና ዓላማ ከግብ የሚያደርስ የትኛውንም አመራጭ ዘዴ ማንም ሰው በራሱ ፈጠራ መጠቀም ይቻላል ።
በዚህም መሠረት ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች ፣ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች ፣ የማህበረሰብ አንቂዎች ፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሚካሄደው የበይነ መርብ ዘመቻ እንድትሳተፉና የሚመለከታችሁን ተግባራት እንድታከናውኑ በአክብሮት እንጠይቃለን።
” ጳጉሜን ፤ ፍትሕ ለግፍ እስረኞች ! “
🖌 የፔቲሽን /የፊርማ መሰብሰቢያ ሊንክ ፦
https://bit.ly/3yJCcVz
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ድረ-ገጾች
Web: https://www.balderasfordemocracy.com/
youtube: https://cutt.ly/AjkRd8D
Facebook: https://www.facebook.com/Balderas.Ethio
Twitter: https://twitter.com/BalderasAddis
Telegram: https://t.me/balderasEth
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን ችሎት በመድፈር ጥፋተኛ በማለት በ4 ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የሚታወስ ነው ።
ሆኖም ፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ውድቅ እንዲሆን በቀረበው ይግባኝ መሠረት ፤ይግባኙን የመረመረው ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎች በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የቅጣት ውሳኔ ሦስት ወር በመቀነስ በአንድ ወር እስራት ውሳኔ ሰጥቷል ።
በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፤ ከችሎት ዘገባ ጋር በተያያዘ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ፣ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እንዲሁም አሐዱ ራዲዮ ” የተሳሳተ እና ዘገባ እና ጽሁፍ ” በማቅረቡ እና ችሎት መድፈር ህግ ተላልፋችኋል በማለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፖሊስ በላከው መጥሪያ መሰረት ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍ/ቤት ቀርበዋል።
ፍ/ቤቱ የክስ ዝርዝር በችሎት ላይ እንደገለጸው 1ኛ ተጠሪ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ” መንግሥት በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የመሰረተው ሀሰተኛ ክስ በአስቸኳይ ይቋረጥ ” በሚል የፍርድ ቤት የዳሰሰ ጽሁፉ ውስጥ የተሳሳተ መረጃ ተላልፏል በማለት ሲሆን።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሽ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ከአሐዱ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ባደረጉበት ወቅት የሰጡት አስተያየት ጋር ተያይዞ ” ችሎት የፓለቲካ ችሎት ነው” የሚል አንድምታ ያለው ቃለ መጥይቅ፤ አድርጋችኋል በማለት “የችሎቱ ገለልተኝነት ” ጥያቄ ውስጥ የሚያስግባ ዘገባ ተሰርቷል በማለት ፍ/ቤቱ የክስ ዝርዝሩን በችሎት ገልጿል ።
1ኛ ተጠሪ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው የዳሰሳ ጽሁፉን እንደፃፈ ፣ በችሎት ሂደት የታዘበውን መዘገቡ እና ለዘገባው የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደተጠቀመ ፤ እንዲሁም የመረጃ ምንጮችን ከሙያው አንፃር ለመግለፅ እንደማይገደድ ለፍ/ቤቱ ምላሽ ሰጥቷል ። የእነ እስክንድር ጠበቃ የሆነው ቤተማርያም አለማየሁ በእነ እስክንድር ጉዳይ ከአሐዱ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረጋቸውን በማመን በቃለ መጠይቅ ወቅት የሰጠውን አስተያየት ሙሉ ቃል በአሐዱ የቀረበ ባይሆንም ፣ አቶ ዛዲግ አብርሃም ለቢቢስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “የፖለቲካ እስረኛ” የለም ማለታቸውን አስመልክቶ ከእሳቸው ተቃራኒ ሃሳብ ገልጫለው ይህ ደግሞ ከችሎት እና ከዳኞች ጋር በተያያዘ ፤ በተለይ ከዚህ ችሎት ጋር በቀጥታ የተገናኘ አስተያየት አልሰጠሁም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ።
አሐዱ ራዲዮ በተወካይ (በጠበቃ አማካኝነት) በሰጠው ምላሽ ከጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ጋር ቃለ መጠይቅ መደረጉ ፣ ሆኖም በኤዲቶሪያል መሉ ዘገባው አለመታየቱን ለችሎት አስረድቷል ።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ምላሽ ከሰማ በኋላ ፤ 1ኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ፤ ዛሬ ታስሮ በነገው ዕለት የቅጣት ማቅለያ ይዞ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ለነገ ነሐሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት ለብይን ቀጠሮ ሰጥቷል ።
ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ችሎት በነፃ አሰናብቷቸዋል። አሐዱ ራዲዮን ችሎት በቢሮ እንደሚያናግራቸው በመግለጽ የክስ መዝገቡን አቆይቶታል።
ይህ ችሎት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ በማለት ፤ የምስክሮች አሰማም ሂደት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚ እንዲሆን በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት
ምስክሮችን ለመስማት ጥቅም 4 ፣ 5 ፣ 8 ፣ 9 እና 10 ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ እንዲያሰማ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ‘የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባና በዝግ ችሎት ይቅረቡ ወይስ በግልፅ ችሎት ይሰሙ’ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ነው። ትናንት ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበረው ችሎት መዝገቡን አለመመርመሩን ጠቅሶ ለዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ማሸጋገሩ ይታወሳል።
ይህንኑ የምስክሮች አሰማም ሂደት በተመለከተ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በግልፅ እንዲ መሰክሩ ከዚህ በፊት መፍረዳቸው አይዘነጋም። የዛሬውን ችሎት የመራው ሰበር ሰሚ ችሎትም ጉዳዩ ከዚህ በፊትም የቀረበለት ሲሆን ራሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንዲወስን መልሶ ወደ ታችኛው የፍርድ ቤት ርከን መላኩ ይታወሳል። የእስር ፍርድ ቤቱ በበኩሉ በጠቅላይ ፍርድ ቤት አጋጅነት ያቋረጠውን የምስክሮች አሰማም ሂደት ለመቀጠል ለሚቀጥለው ዓመት ማለትም ለጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በተለያዩ ጊዜያት በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተካሄዱ ባሉ ክርክሮች የኅሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ በአካል ቀርበው አያውቁም። ከዚህ ቀደም ከወራት በፊት በተደረጉ ክርክሮች ከፊሎቹን ካሉበት ወህኒ ቤት ውስጥ ሆነው በፕላዝማ ቴሌቪዥን ቀርበው ተከራክረዋል። ከሰሞኑ እየተደረጉ ባሉ ክርክሮች ደግሞ ፈፅሞ እንዳይቀርቡ ተደርጓል። በዚህም እነ እስክንድር ለችሎቱ ማስረዳት የሚገቧቸውን ጉዳዮች እንዳይናገሩ ታፍነዋል። እማኞች በግልፅ ችሎት ወይም በዝግና ከመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክሩ ይፈርዳል የተባለው ችሎት ራ፤ ራሱን ደብቆ እየፈረደ ይመስላል። ምክንያቱም በእነዚህ ችሎቶች ታዳሚያን የሉም፣ ጋዜጠኞች የሉም፣ ራሳቸው ተከሳሾች የሉም፣ ለወትሮው የሚታደሙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ሌሎች ግለሰቦችና ድርጅቶች የሉም። ጉዳዩ የደብዳቤ ልውውጥ ሆኗል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ (5 ሰዎች) ላይ በከፈተው ዶሴ ያሉትን የሰው ምስክሮች እንዲያሰማ አዝዟል። በመሆኑም ሀምሌ 8፣ 9፣ 14፣ 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም. 21 ምስክሮችን በግልፅ ችሎት እንዲያቀርብ ተወስኗል። በዚሁ መሰረት ቢጠበቅም ዐቃቤ ሕግ (ዐቃቤ መንግሥት) የመጀመሪያዎቹን ሁለት ቀናት ምስክር ያሳቀርብ ብቻውን ቀረበ። ከዚህ ቀጥሎ አምስቱንም ቀናት ብቻውን ቢቀርብና ማስመስከር ባይችል ኖሮ በሌላ ጊዜ መልሶ የማንቀሳቀስ መብቱ ተጠብቆለት ለጊዜው ክሱ ተቋርጦ መዝገቡ ይዘጋ ነበር።
የነፃነት ታጋዮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌም ከእስር ይፈቱ ነበር። ሆኖም በሦስተኛው ቀን ማለትም ሀምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ዐቃቤ መንግሥት ተከሳሾችና ጠበቆቻቸው በሌሉት አስወስኖ የእግድ ደብዳቤ ይዞ ቀረበ።
ሃምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ‘ምስክር አሰማ የምባል ከሆነ ፍትሕ ይጓደላል’ ሲል ያቀረበውን አቤቱታ በፊርማቸው ይዘው ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረቡት ተመስገን ላጲሶና ደመላሽ ኢጀታ ናቸው። ተመስገን ላጲሶ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ወንጀሎች ዳይሬክተር ነው። ይህ ሰው ከጀርባ ቢኖርም ለችሎቶች ግን እንግዳ ነው። #አብይ መርዕድ የተባለው የአምቦ ተወላጅ ‘እንደዚህ አይነት የሀሰት አቤቱታ አላቀርብም። አልፈርምም’ በማለቱ ነው ተመስገን የመጣው። አብይ መርዕድ በዚህ ባህሪው ለባልደረቦቹ ቤትና መኪና ሲሰጥ ዳረንጎት እንዳልደረሰውም ሰምቻለሁ።
ይኸው ነው፤ በጥቅማጥቅም እየተደለለ የሚፈርድና የሚከራከር ባለሙያ ሲጠፋ አለቆች ይመጣሉ። ሁሉም አሻፈረኝ ቢሉ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ተብየ)፣ ብርሃነ መስቀል ዋቅጋሪ (የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ተብየ) እና መዓዛ አሸናፊ (የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ተብየ) ይመጣሉ። ሦስቱም እምቢ ቢሉ የውንብድና ስርዓቱ ተንኮታኩቶ እስካልጠፋ ድረስ ከሳሽም ፈራጅም ሆኖ አብይ አሕመድ ራሱ ካባ ደርቦ መምጣቱ አይቀሬ ነው።
የዐቃቤ ሕግን አቤቱታ ተቀብለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ሦስት ዳኞች ማለትም ሸምሱ ሲርጋጋ፣ ዋዚሞ ዋሲራ እና ደረጀ አያና አፀደቁት። በመሆኑም ሀምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ዐቃቤ ሕግን በምስክሮች ፈንታ የእግድ ደብዳቤ አስይዘው ወደ እስር ፍርድ ቤቱ ላኩት። የእስር ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 260175 ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ያሳለፈው ውሳኔ ታግዶ ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተመለሰ።
የእነ ሸምሱ ሲርጋጋ ችሎት በዐቃቤ ሕግ አቤቱታ ላይ የጠበቆችን መልስና የመለስ መልስ በፅህፈት ቤት ለመቀበል ለሀምሌ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። መቼም መለዋወጥ ዋነኛ መገለጫቸው ሆኗል። በዚሁ መሰረት የእነ እስክንድር ጠበቆች አስቀድሞ እንደታዘዘው በፍርድ ቤቱ ፅህፈት ቤት ተገኝተው የዐቃቤ ሕግን አቤቱታ ለማየትና መልስ ለመስጠት ቢጠይቁም ተከለከሉ። ‘ለተከሳሾች ለራሳቸው እንጂ ለጠበቃ አንሰጥም’ በሚል ተባረሩ። ፍርድ ቤቱ እነ እስክንድርን ጠበቃ አልባ ለማድረግ ሞከረ።
እስረኞች የማይቀርቡበት የሀምሌ 26ቱ ችሎት ለዛሬ ነሀሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀጠረ። ነገር ግን ዛሬም መዝገቡ ሳይገለጥ ለነገ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። ከላይ የተጠቀሱት ሦስት አውታታ ዳኞች ለዚህ የሰጡት ሰበብ “መዝገቡን አልመረመርንም” የሚል ነው። ለመሆኑ ምን እየሠሩ ነው ያልመረመሩት? ሥራን ያለ መሥራት ዋልጌነት ሊያስቀጣስ አይገባም ወይ? በእነርሱ ዋልጌነት አራት ንፁሃን ዜጎች ፤ ያውም ኢትዮጵያ ላለችበት ወቅታዊ ችግር ከፍተኛ የመፍትሔ አመንጭነት አቅም ያላቸው ታላላቅ ፖለቲከኞች እስር ቤት መቆየታቸው አያሳስባቸውም ወይ?
ከዚህ በፊትም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ‘መዝገቡን አልመረመርኩም፣ ዳኞች ተሟልተው አልቀረቡም፣ ፕላዝማ ተበላሽቶብኛል’ በማለት ችሎቶችን ሲያጓት ቆይቷል። የወንበዴ ጥላ ከለላ ሆኖ ንፁሃንን ማንገላታት እስከ መቼ?