በጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እስር ላይ ሦስት ወር ተቀነሰ !

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን ችሎት በመድፈር ጥፋተኛ በማለት በ4 ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የሚታወስ ነው ።
ሆኖም ፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ውድቅ እንዲሆን በቀረበው ይግባኝ መሠረት ፤ይግባኙን የመረመረው ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎች በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የቅጣት ውሳኔ ሦስት ወር በመቀነስ በአንድ ወር እስራት ውሳኔ ሰጥቷል ።