ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE

የሕክምና ባለሙያዎችን ጥያቄ እና እስር አስመልክቶከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
በሀገራችን በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሀገራት የሕክምና ት/ቤቶች (Medical Colleges) ለመግባት፣ ብዙ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል። ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃም የሕክምና ት/ቤት የሚገቡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተናን በከፍተኛ ውጤት የሚያልፉ ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች፣ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸውም ሆነ በትምህርቱ ይዘት ምክንያት ከአብዛኛው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በላቀ ሁኔታ የትምህርት ጫና የሚበዛባቸው እና ይህንንም ተወጥተው ለመመረቅ የሚደርሱ ናቸው። ከሌሎች የትምህርት […]

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በአማራ ክልል የተገደሉ ከ60 በላይ ንፁሀንን ሞት በተመለከተ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በየትኛውም ደረጃ እና መልክ የሚደረጉ ጦርነቶች በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን “የጦርነት ህጎችን” ማክበር ይገባቸዋል። ለአብነትም በ1949 እ.ኤ.አ የፀደቀው አራተኛው የጄኔቫ ስምምነት አንቀፅ 3፣ 27 እና 32 ላይ፣ እንዲሁም በ1977 እ.ኤ.አ በተደነገጉት ሁለቱ ፕሮቶኮሎች፣ ፕሮቶኮል I አንቀፅ 48፣51፣57 ፤ ፕሮቶል II አንቀፅ 13 ላይ ‘ንፁሀን ላይ ምንም አይነት ጥቃት እንዳይደርስ እና ከጥቃትም እንዲጠበቁ’ ያስጠነቅቃሉ። ነገር […]

በአፋር ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይርተሰጠ መግለጫ በጥር 22/2017 ዓ.ም በአውሲ ራሱ ዞን ኤሊዳር ወረዳ ኪያሩ ቀበሌ በደረሰ የድሮን ጥቃት ቢያንስ ስምንት የሚሆኑ የአፋር ወገኖቻችን መሞታቸው ታውቋል። ጥቃቱ የተፈፀመው በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ድሮን መሆኑን የጅቡቲ መንግስት ያመነ ሲሆን፣ ነገር ግን በራሱ ግዛት ላይ እንደተፈፀመ አሳውቋል። እንደ ምክንያት የጠቀሰውም የሽብር ጥቃትን ለመከላከል እንደሆነ ገልጿል። የአፋር ክልል ነዋሪዎች […]

በሕዝብ ማታገያ ድርጅት ላይ በፈጠራና በሀሰተኛ ወሬ የሚሰነዘር የስም ማጥፋት፣ የሕዝብን ትግል ከማደናቀፍ ተለይቶ አይታይም!
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እስከ ነሀሴ 2016 የመጨረሻ ሳምንት ድረስ በክልል አቀፍ ፓርቲነት ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል። ሆኖም ፓርቲው ወደ ሀገር አቀፍነት ማደግ እንዳለበት በጠቅላላ ጉባኤ ታምኖበት ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ፣ ከ6 ክልሎች ከሚጠበቅበት ከአስር ሺህ ፊርማ በላይ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ለምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲነቱ እንዲፀድቅለት ጥያቄ አቅርቦ፣ የቀረቡት ፊርማዎችም […]

ከስራቸው የተፈናቀሉ ሰራተኞች በአስቸኳይ ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሱ
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የአንበሳ አውቶቡስ እና የኢትዮ ፖስታ አገልግሎት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በግፍ ከስራቸው እየተባረሩ መሆናቸውን ባልደራስ ከደረስው የህዝብ ቅሬታ አረጋግጧል፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንት ብቻ ከአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከ480 በላይ ሠራተኞች አለ አግባብ ከስራቸው ሲባረሩ ፣ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ደግሞ እንደዚሁ […]

በንፁሐን ሞት እና ሰቆቃ የሚተከል አሻራ፣ የሚፀና ወንበር የለም
በንፁሐን ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከባልደራስ ለአውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሠጠ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሶስት አሰርት ዓመታት በተለይ ደግሞ ባለፉት ስድስት ዓመታት ከፀሐይ በታች በሰው ልጆች ላይ ያልተፈፀመ ግፍ የለም፡፡ የአማራ ሕዝብ በስርዓት እና በመዋቅር በተደገፈ ሁኔታ የእልቂት ሰለባ መሆኑ የአደባባይ እውነት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ይሁን እንጂ ሰውን እንደ ሰው በማይመልከት የነገድ ስርዓት ውስጥ የሚኖር […]

የአዲስ አበባ ህዝብ የብልፅግና መንግስት የቤት ፈረሳ ይበቃል ሊል ይገባል
ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ የኦህዴድ ብልፅግና የጎጥ ፖለቲካ ወላጅ አባቱን ተክቶ አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ ስድስት አመታትን አስቆጥሯል። በዚህ ሁሉ ጊዜ ከሀሰት ትርክት የተወለደ የጥላቻ ፓለቲካን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች፣ በከፋ መጠንና በተለያየ ስልት ሳያቋርጥ ሲያራምድ ቆይቷል። እንደ ኦሀዴድ/ብልፅግና ያሉ ጥንፈኛ የነገድ ፖለቲከኞች ፖለቲካቸውን የተቃኜው የዛሬ 40 እና 50 ዓመታት በፊት በፈጠሩት የሃስት ትርክት ላይ […]
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና አቶ ካሳሁን ደስታ እስር ህገ ወጥ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ እንዲፈታቸው ባልደራስ አበክሮ ያሳስባል
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና የፓርቲው ንቁ አባልና ጉዳይ አስፈፃሚ አዲስ አበባ ውስጥ ትላንት ህዳር 03/2015 ዓ.ም. በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል፡፡ በቅድሚያ የታሠሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ሲሆኑ ለእሳቸው ስንቅ ለማቀበል አቶ ካሳሁን ደስታ በሄዱበት ወቅት እሳቸውንም ፖሊስ አስሮ አስቀርቷቸዋል። የአዲስ አበባ መሥተዳድር እና የኦህዴድ/ብልጽግና መር መንግሥት ቆሜለታለሁ ከሚለው […]