ኢንጅነር ዓለማየሁ
ኢንጅነር ዓለማየሁ
#የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የምርጫ ወረዳ 19
የን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወገኔ ምርጫህ ባልደራስን ይሁን !!!
ኢንጅነር ዓለማየሁ ንጋቱ እባላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የምርጫ ወረዳ 19 የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ነኝ። ኢኮኖሚስትና የብዙ ባለሙያ ባለቤት ነኝ። የአዎንታዊነት መጽሐፍ ደራሲም ነኝ። የሰው ልጅ ለዓላማ የተፈጠረ በመሆኑ ለዓላማ ሊኖር ይገባዋል እላለሁ። ለራስ ብቻ ሳይሆን ስለሌሎች መኖርን ነው፡፡ በተለይ ከዛሬ አርባ ዓመት ገደማ በነፍስ ወከፍ ገቢ የምንበልጣት ቻይና የመመንደግ ሚስጢሮን ለመረመረ ለምን? እኛስ በማለት እብሰለሰላለሁ ፤ ሠላም፣ ሁሉ ዓቀፍ ዕድገት፣ ዴሞክራሲ፣ መግባባትና አንድነት ለምን ጎደለን ? እውነትን አክብሮ ለእውነተኞች ዘብ መቆም ለምን አጠረን ብዬ እጠይቃለሁ ፡፡ ለምላሹም ፣ ለመፍትሄው የበኩሌን ለመወጣት ተዘጋጅቻለው።
መዲናችን አዲስ አባባ ከሌሎች በርካታ የዓለም ከተሞች ጋር ስትነፃፀር ጉድለቶ ልቆ የሚታይ መሆኑን እርግጥ ነው ፡፡ ይህ ጭምር ነው ባልደራስን እንድቀላቀል ጉልበት የሆነኝ፤ የተመቻቸ ህይወቴን እንድፋታ ያገዘኝ፣ ለዓላማ ለመኖር እንዲሁም ምሳሌነትን እንዳከብር የገፋፋኝ ፤ ትላንትስ ትላንት ሆኖ ዛሬን ለግሶ ነጎደ፤ ዛሬ ግን አዲስ ታሪክ ልንጀምር ይገባናል።
እኛ ኢትዮጵያውያን በሁለዓቀፍ ዕድገት መላቅ ሲገባን በጥቂቶች ስንጎተት ከርመን ዛሬም ድህነትን መሻገር ከብዶን ተገኝተናል፡፡ ሊያንገሸግሸን እንዲሁም በቃን ልንል ጊዜው ጠይቆልና ለሁሉ ዜጋ የምትበቃ ውብ አገርን ለመፍጠር፤ መነሳሳት፣ መተባበር፣ መመጋገብ እና አንድነት ይሻለናል ከሚለው የእውነት ቁንጮው ባልደራስ ጋር መስራት አስገድዶን ነው እኔን ጨምሮ በርካታ ሙሁራን በተለይ ለታችኛው ማህበረሰብ በእውነት የሚሞግተውን ፓርቲ የተቀላቀልነው ፡፡
በጥቂቱ ነፃነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የዜጎች እኩልነት፣ የግል ሀብት ባለቤትነት እንዲከበር፡፡ የሥራ አጥነት እንዲሁም፣ የኑሮ ውድነት እንዲቀንስ፤ የፖለቲካ ሹምነት በብቃት፤ የጎሳ ፖለቲካ ደግሞ በዜግነት ፖለቲካ እንዲተካ የምትሻ ውድ የተከበርከው የን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወገኔ ምርጫህ ባልደራስን ይሁን፡፡ ለእውነት ቆመህ፤ ከለውጥ ኃዋሪያቶች ጎን ሆነህ የነገይቷን ኢትዮጵያ ተጋግዘን እንገንባ፡፡
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ