አምሃ ዳኘዉ
አምሃ ዳኘዉ
#የካ ክ/ከ ምርጫ ክልል 28
አዲስ አበባ በሞግዚት ሳይሆን የልብ ትርታህን በሚያዳምጡ የከተማዉ ነዋሪዎች ልትተዳደር ይገባል !!
አምሃ ዳኘዉ ተሰማ እባላለሁ። በመጪው 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፖርቲን በመወከል በአዲስ አበባ የካ ክ/ከ ምርጫ ክልል 28 ለሕ/ተ/ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ ሁኜ ቀርቢያለሁ ። ምርጫ ክልል 28 ወረዳ 9 -10 -11 -12 -13 – 14ን የሚያጠቃልል ሲሆን እነዚህ ወረዳዎች ከእስራኤል ኢምባሲ እስከ ጣፎ እና ሲ ኤ ም ሲ ኣያት ከመንገድ በላይ ያለዉን አካባቢ የሚያካትት ነዉ።
በኢኮኖሚ ልማት የማስተርስ ዲግሪ አለኝ። በዚህ ሙያ የሰላሳ ሰባት አመት የሥራና የአማካሪነት ልምድ አለኝ። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የአርባ ሰባት አመት ተሳትፎየ የስልሳዎቹ ትውልድ በሃገራችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አስተሳሰብ ላይ ያስረጸዉ አፍራሽ ተጽእኖ አራማጅ ሁኜ በሃገሬ ላይ የፈጸምኩትን በደል ለመካስ በታላቅ ቁጭት ተነሳስቻለሁ።
የሃገራዊ ብሄረተኝነት እና ዘዉጋዌ ብሄረተኝነት በኢትዮጵያ – ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር የቀረበ የመፍትሄ ሃሳብ የሚል ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን በምን መንገድ ማልማት ይቻላል የሚል በእንግሊዘኛ የተጻፈ የሁለት መጽሓፎች ደራሲ ነኝ። ላለፉት 30 ዓመታት አዲስ አበባ አንተ/ች ባልወከላችሆአቸው ገዢዎች እጅ ውስጥ በመቆየቷ ልጆቻችሁ ከኢኮኖሚ፣ ከማህበራዊ እና ከፓለቲካ እንቅስቃሴዎች በመገፉታቸዉ ያጣችሁትን ሁለንተናዊ ጥቅም የምታስመልሱበት ጊዜው አሁን ነው።
ይህንንም ማሳካት የምትችሉት በየአካባቢያችሁ ወደ-ተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የምርጫ ካርዳችሁን በመውሰድ ፤ ድምጻችሁን የእናንተ መገፋት እና ሰቆቃ ለወለደው ለባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በመስጠት ብቻ ነው !
አዲስ አበባ በምስለኔ ሳይሆን በመረጣችሆቸዉ የከተማዉ ነዋሪ ዜጎች እንድትተዳደርና ተረኞች ከጋረጡብን የሕልውና አደጋ ሁላችንም እንድንድን ለማድረግ የሚችሉ ቁርጠኛ አቋም ያላቸዉን እጬዎች ባልደራስ ለእውኘነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አቅርቦላችኈልና፤ ባልደራስን እንድትመርጡ በታላቅ ትህትና ጥሪዬን አቀርብልሃለሁ።
ባልደራስን መምረጥ አዲስ አበባን ከፖለቲካ አፈና እና ከኢኮኖሚ ብዝበዛ ማላቀቅ ነው !!!
ባልደራስን መምረጥ ለፖለቲካ እና ነጻነት አብሮት ለሚሄደዉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚደረግ ምርጫ ነዉ !!
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ !!!