አብን የባልደራስመኢአድን ጥምረት ሊቀላቀል ነው
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የባልደራስ- መኢአድን ጥምረት በመቀላቀል መጭው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) እና ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም የመራጮች ድምፅ እንዳይከፋፈል ያግዛል፡፡ ሦስቱ ፓርቲዎች ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት እየሰሩ ሲሆን በተለይ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፡፡ ከተማዋ የሁሉም ነዋሪዎቿ እንደሆነች ያምናሉ፡፡ በአዲስ አበባ ላይ የኦሮሞ ልዩ ጥቅም እንዲሰጠው የሚደነግገውን አፓርታይዳዊ አዋጅ ይቃወማሉ፡፡ የሦስቱ ፓርቲዎች ጥምረት አስቀድሞ በሕዝብ፣ በፓርቲዎቹ መካከለኛ አመራሮች አባላት ዘንድ ሲቀርብ የቆየ ጥያቄ ነው፡፡