ፍርድ ቤቱ መፍረድ አልቻለም !!
ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ ወይስ በድብቅ የሚለውን ፍርድ ለመስጠት ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለወራት ጉዳዩን ይዞ ከቆየ በኋላ ” የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ግራና ቀኝ መርምሮ ውሳኔ ይስጥ ” በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
ትዕዛዝ የተሰጠው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከዚህ ቀደም መስከረም 4 ቀን 2013 ግራና ቀኝ አከራክሮ ” ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ ” በማለት ብይን በመስጠት ከሳሻ ዐቃቤ ህግ ምስክሮችን እንዲያሰማ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር ።
ይሁን እንጂ ዐቃቤ ህግ በምስክር አሰማም ሂደት ላይ ይኽው ፍ/ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃውም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ጠይቋል።
ይግባኝ የተጠየቀው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ፍርድ መፍረድ አልቻለም ። ጉዳዮን መልሶ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከዚህ ቀደም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ።
በዚሁ የቀጠሮ ቀን ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም የግፍ እስረኞች እነ እስክንድር ነጋ ልድታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ።