ብሄራዊ መግባባት ሽብር ባልፈጸመ ሰላማዊ ታጋይ ላይ የሽብር ክስ በመመስረት ህጉን የፖለቲካ ተገዥ በማድረግ አይገኝም!!!

 “እውነት ከአንባገነኖች ክንድ ትበረታለች”!እናት አገራችን ውዲቷ ኢትዮጵያ ከአያት ቅድም አያቶች አጥንት ፍላጭ ተማግራ፣ አፈሯ በደማቸው  ተለዉሶ ተቦክቶና ተጋግሮ ለሺዎች ዘመን የቆመች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ ነገዶች ባህል ከባህል፣ሃይማኖት ከሃይማኖት ነገድ ከነገድ ተስበጣጥሮ ያቆማት የውህድ ማንነት ተምሳሌት ሀገር ናት፡፡ ይህም በልጆቿ ተጋድሎ ለዘመናት ከውጭ ወራሪ ሀይል ተጠብቃ በመቆየት የጥቁር ህዝብ ፈርጥ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ሆኖም በልጆቿ አጥንትና […]