ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
የሐዘን መግለጫ
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት የሰማነው፣ በጥልቅ የሐዘን ስሜት ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣የኢትዮጵያ፡ቁዋንቁዎችንና ፡ሥነጽሑፍ እንዲኹም ታሪክ አስመልክተው ፣አያሌ የጥናትና የምርምር መጻሕፍትን ያበረከቱ ብርቅ፡ኢትዮጵያዊ፡ምሁር፡ነበሩ።የቋንቋ ፣የሥነ ጽሑፍ፣የታሪክና የሥነመለኮት ሊቁ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ በተለያዩ አገራዊና አህጉራዊ የፖለቲካ እድገት አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ይሰጡዋቸው፡በነበሩቱ በሳል ሀሳቦቻቸው እና ትችቶቻቸው ይታወቁ፡ነበር።እኚህ ሀገራቸውን ወዳድ፣ ዓለም አቀፋዊ ምሁር […]

በአዲስ አበባ በ218 የምርጫ ጣቢያዎች የታዩ ተግዳሮቶች የዳሰሳ ጥናት ውጤት !
1. የጥናቱ መሰረታዊ ሀተታ (Statement of the Problem)እንደ “UDHR“(1948) ክፍል 3 አንቀፅ 21 ድንጋጌ መሠረት የመንግሥት ሥልጣን መሰረቱ የሕዝቡ ፈቃድ ይሆናል፤ይህ ፈቃድም በየተወሰነ ጊዜ በሚደረግ እውነተኛ ምርጫ አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን ምርጫም በምስጢራዊ የድምጽ አሰጣጥ ወይም መሰል ነፃ ሂደት ሁሉን አቀፍና እኩል አሳታፊ በሆነ መንገድ የሚካሄድ ይሆናል።በተመሳሳይ ሁኔታ “ICCPR“ (1966)አንቀጽ 25 ድንጋጌ መሰረት እያንዳንዱ ዜጋ በዘር፣ቀለም፣ፆታ፣ቋንቋ፣ሐይማኖት፣የፖለቲካ […]
ሀገርን የማዳን ጥሪ – የመጨረሻው መጀመሪያ
ከባልደራስ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተሰጠ ሀገርን የማዳን ጥሪ (Balderas Support in North America )ለብዙ ሺህ አመታት በአባቶቻችን መስዋዕትነት የቆየችው ሀገራችን ዐይናችን እያየ እጃችን ላይ ሳትፈርስ ሁላችንም በአንድ ላይ ልንቆም ይገባል!የተከበራችሁ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን የዛሬ ሦስት ዓመት በአገራችን የተካሄደው ለውጥ በልባችን ውስጥ ሰንቆት የነበረው ተስፋ ከህሊናችን በቀላሉ የሚጠፋ […]
የሀዘን መግለጫ
ባለፉት ሁለት ቀናት በሰሜን ሸዋ መንግስት-መር በሚመስል መንገድ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ ጥልቅ ሀዘን የተሰማው ሲሆን በተሰማን ጥልቅ ሀዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም እንደማይኖር ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በሞት ለተለዩን ወገኖቻችን ፈጣሪ እረፍትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን፤ ለተጎዱ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡

የሀዘን መግለጫ !
በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል ዕጩ በአቶ በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር የተደረገውን የግድያ ወንጀል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እጅጉን እንደሚያወግዘው እየገለፀ ለሟች ቤተሰብ እና ለባልደርቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ዘመቻ ይቁም!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በአፋር አርብቶ አደር ወገኖቻችን ላይ በተፈፀመው ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የአፋር ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን ይመኛል። ኦሕዴድ/ብልፅግና ኢትዮጵያን ከቻለ አፍርሶ በራሱ ቀለም እንደገና ለመሥራት ይህ ካዳገተውም እንደ ሐረሩ የራስ መኮንን ሀውልት አፈራርሶ ለመተው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እናምናለን። ቅርሶችን ጨምሮ ነባር የኢትዮጵያ መገለጫዎችን የማፍረስ እና አንዳዶችን በአዲስ የመተካት […]

ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!
ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!ከሁሉ አስቀድመን በአገራችን በኦሮምያ ክፍለ-ሃገር በተለያየ ወቅት በተደጋጋሚ በተፈጸመ ጥቃት ፤ በንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና ኦነግ ሸኔ በተባለ የዳቦ ስም የተሰጠው ገዳይ ቡድን አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ እውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገልጻል!የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡በንጹሃን […]
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በጽኑ እናወግዛለን !
ባለፉት ዓመታት በተለይ “ለውጥ” መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በዜጎች ላይ የሚፈፀመውን የዘር ፍጅት ወንጀል በአይነቱ እና በመጠኑ እየጨመረ መጥቷል ። ለዚህም ዋንኛው ምክንያት አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት እንደሆነ ብዙ አስረጂ የሚሻ ጉዳይ አይደለም ።በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ የተፈጸመው የዘር ፍጅት ወንጀል ከዚህ ቀደም በክልሉ ሲፈጸም ከነበረው አረመኔያዊ […]