ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
በኦሮሚያ ክልል በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፕሮግራማዊ ተልእኮ እየተመራ ያለው የአማራን ዘር የማጥፋት ኢ-ሰብዓዊና አፀያፊ ድርጊት ሊቆም ይገባል
ቀን 29/03/2015 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ የሚኖሩ በኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል እና በሸኔ ሽብርተኞች ጥምር ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሐን በግፍ መጨፍጨፋቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአማራ ተወላጆች በየጊዜው በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በአማራ ተወላጆች ላይ በተካሔደው ጭፍጨፋ ኦነግ ሸኔ የተባለው ሽብርተኛ ቡድን ግንባር ቀደም መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ ግን የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ተሳታፊ እንደሆነ በገሃድ […]
የደራ አማራን የዘር ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
የሰላም ድርድሩን አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ።
በህወሓትና በኦህዴድ/ብልፅግና መሃል ያለው የስልጣን ሽኩቻ እንጅ የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት እንዳልሆነ ይታወቃል። በሶስተኛው ዙር ጦርነት ወቅት በኦህዴድ/ብልፅግና መንግሥት በኩል የህወሓትን የመዋጋት አቅም ሙሉ በሙሉ እንዲንኮታኮት ማድረግ መቻሉ በገሃድ ታይቷል። ይሁንና በሁለት ምክንያቶች ኦህዴድ/ብልጽግና በጦርነት ያገኘዉን ድል ያረጋገጠለትን የደቡብ አፍሪካ ስምምነት በናይሮቢ ስምምነት እየሻረዉ እንደሆነ የሰሞኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ኦህዴድ/ብልጽግና የህዉሃት ወታደራዊ/ፖለቲካዊ አደረጃጀት እንዳይከሰም የሚፈለገባቸዉ ምክንያቶች ሁለት […]
ለባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ
ቀን፡-03/02/2015 ዓ.ም ቅዳሜ ጥቅምት 5/2015 ከ6:00 እስከ 10፡00 ሰዓት የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴም ሆነ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የጠሩት በፓርቲው የጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ስብሰባ የሌለ መሆኑን ለፓርቲያችን አባላት በሙሉ እንገልፃለን፡፡ በጽ/ቤታችን የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ አለ ብሎ የጠራው ህገ ወጡ አፍራሽ ቡድን መሆኑ ታውቆ፣ አቶ እስክንድር ያቋቋመውን እና በርካታ አባላት መስዋእትነት የከፈሉበትን ፓርቲ ህልውና ለማስቀጠል […]
የወቅቱን የሃገራችንን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ሁኔታ በማስመልከት ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በእርስ በርስ ጦርነት ፣ በርሃብ፣ የነገድ ፖለቲካ ባስከተላቸው ቀውሶች፣ በፍትህ እጦት፣ በኑሮ ውድነት፣ ወዘተ… እና በሌሎችም አሳዛኝና አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገጠሟት እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ወቅቶች መሃከል ይህ አሁን ያለንበት እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምዕራባውያን ሀገራት ከረጅም ጊዜያት አንስቶ ኢትዮጵያን በእነሱ ተጽዕኖ ሥር ለማድረግ ‹‹አማራን ማዳከም ይገባል›› […]

” የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም። ድምፅ ተዘርፏል”
የስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለይ የአዲስ አባባ የቅድመ ምርጫ ሂደት እና የድህረ ምርጫ የነጻ፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ መሆኑን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል። “ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ዘርፈውታል። ይህም በመሆኑ በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለው” ብሏል ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የምርመራ ውጤት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ […]
በምርጫው ጉዳይ ላይ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛ አገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ በማሰባሰብ አጠናክሮ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ፣ በድምጽ አሰጣጡ እና ቆጠራው የነበሩ ችግሮችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ፓርቲያችን አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ […]
ኢትዮጵያ መቼ ይሆን ነፃ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የሚኖራት ?!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ፍትህ እንዲሰፍን ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ፣ አድሎአዊነትና ዘረኝነት እንዲወገድ፣ሕዝብ ከመፈናቀልና ከድህነት እንዲላቀቀቅ፣ አዲስ አበባ የራስ ገዝ አስተዳደር እንድትሆን እና ሌሎችም ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሰፍኑ የሚያስችል ሥርዓት ለማምጣት ጠንክሮ ሠርቷል፤እየሰራም ነው፡፡የሃገሪቱ መሪ ‹‹ከባልደራስ ጋር ግልጽ ጦርነት እንከፍታለን›› እያሉ በተናገሩበት ወቅት እንኳን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከመታገል ቁርጠኛ አቋሙ ወደ ኋላ አላለም፡፡ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ […]