የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል

በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆች የቀረበው አቤቱታ ላይ ፍ/ቤቱ፣ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።
ጠበቆቹ በብይኑ ላይ ቅሬታ ስላደረብን ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን በማለት የህግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ገልፀውልናል።