የግፍ እስረኞቹ እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ ተለቀዋል
የሀሰት ክስ ቀርቦባቸው በግፍ እስር ላይ የሰነበቱት የባልደራስ ፓርቲ የምክርቤት አባላት፣ አቶ ሳሙኤል ዲሜትሪ እና አቶ ፋሲል ማሞ ከነበሩበት የግፍ እስር በዛሬው እለት ተለቀዋል።
ፖሊስ ዛሬ በዋለው ችሎት የግፍ እስረኞቹ ላይ በድጋምል ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ቀናትን የጠየቀ ቢሆንም፣ የግፍ እስረኞቹ ጠበቆች ይህንን ተቃውመው ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን የሰማ ሲሆን፣ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የግፍ እስረኞቹ እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ወስኗል።
በዚህም መሰረት በግፍ እስር ላይ የቆዩት አቶ ሳሙኤል ዲሜትሪ እና አቶ ፋሲል ማሞ ዛሬ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።
የግፍ እስረኞች ይፈቱ!