የግፍ እስረኛው አቶ ካሳሁን ለይደር ተቀጠሩ
በሀሰት ክስ ለታሰሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ስንቅ ለማቀበል እና ለመጠየቅ በሄዱበት በፖሊስ ታግተው እዛው የቀሩት አቶ ካሳሁን ደስታ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በቀጠሯቸው መሰረት ፍ/ቤት ቀርበዋል።
ፓሊስ በዛሬው ችሎት ላይ አቶ ካሳሁን ሌላውን እስረኛ አቶ ናትናኤልን ለመጠየቅ በሄዱበት እንዳሰራቸው ክዷል። ይባስ ብሎም አቶ ካሳሁንን ያሰረበትን ምክንያት ሲናገር ”በአምሀ ደስታ ት/ቤት በነበረው ተቃውሞ ላይ ከኋላ መኪና ይዘው ሲያስረብሹ ነበር” ብሏል። ጠበቃቸው ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በበኩላቸው ደምበኛቸው መኪናም ሆነ መንጃ ፍቃድ እንደሌላቸው እና ማሽከርከርም እንደማይችሉ አስረድተዋል። ይህ ሀሰተኛ የፖሊስ ክስም እንዲመዘገብላቸው ጠይቀዋል።
ፖሊስ የሰነድ እና የሰው ምስክር ለማደራጀት እና ያልተያዙ ግብረአብሮችንም ለመያዝ ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጠይቋል። የግፍ እስረኛው ጠበቃም ክሱ ፍፁም ሀሰት መሆኑን በመግለፅ፣ እስረኛው እስካሁን የቆዩበት 10 ቀናት ለምርመራ በቂ በመሆኑ ፖሊስ የጠየቀው 14 ቀን መፈቀድ የለበትም ብለዋል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ የተከሳሹ የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀዋል። በተጨማሪም የፖሊስ መዝገብ ቀርቦ እንዲታይ ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከሰማ በኋላ መዝገቡን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት በይደር ለነገ አርብ (14/04/2015 ዓ.ም) ለጠዋት 3:30 ቀጥሯል።
በነገው እለት ሁለቱም በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ንቁ-አባላት አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡ ይሆናል።
ፍትህ ለግፍ እስረኞች!
ድል ለዲሞክራሲ!