የሐዘን መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስክንድር ነጋ !
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት በተመለከተ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት የሐዘን መልዕክት ።
“መካሪዬ፣ አባቴ፣ አስተማሪዬ የሆኑት በማረፋቸው በጣም አዝኛለሁ። ጓጉተውለት የነበረውን የዘንድሮ ምርጫ ውጤት አይተው ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃዱ አልሆነም። የሰላም እረፍት ይሁንላቸው። ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ”
እስክንድር ነጋ
ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት