ዜና(News)
ለሚዲያ አካላት የቀረበ ጥሪ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ጋር በመተባበር “የምርጫ 2013 ተስፋና ስጋቶች” በሚል ርዕስ በራስ አምባ ሆቴል ነገ ሚያዚያ 07/2013ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ ውይይት ያካሂዳል።ዝግጅቱ ለሁሉም የብዙሃን መገናኛ ክፍት በመሆኑ ሁሉም የሚዲያ አካላት በሥፍራው ተገኝተው እንዲዘግቡት ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል።
በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት በዛሬው ችሎት ሊዳኝ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ለሚያዝያ 15 ተዛወረ !!
በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚደረገው ችሎት ለዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀጥሮ የነበረው ችሎት ‘ፕላዝማው ተበላሽቷል’ በሚል ለፊታችን ሚያዝያ 15 ቀን ተዘዋውሯል። ይኸው ችሎት ከዚህ በፊት ለመጋቢት 28 ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን ከሦስቱ ዳኞች መካከል አንዱ ባለመገኘታቸው ነበር ለዛሬ የተሸጋገረው። የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከፕላዝማ ይልቅ በችሎቱ ፊት ለፊት […]
“ጣምራ ፌደራሊዝም”
ኢትዮጵያ ብዙህ ስትሆን ብዙሃነትን ማስተናገድ ግዴታዋ ነው፡፡ ብዙሃነት ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓተ መንግሥት ስናስብ የፌደራል ሥርዓቱ ቀዳሚ አጀንዳ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የፌደራል ሥርዓቱን ህጸጾችና በጎ ጎኖች በመገምገም የፌደራል ሥርዓታችን ኢትዮጵያዊ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚነሳው ኣንዱ ዋና ኣጀንዳ ይሄ ሲሆን አዲስ የፌደራል ሥርዓትን ለኢትዮጵያ ያስተዋውቃል፡፡ የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራል ሥርዓት ይባላል፡፡ የፌደራል ሥርዓት ጽንፈኛ የሆነውን ፖለካችንን […]
በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግፉአንን ድምጽ ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ ነው
በዓለም ዙሪያ በተለይም በአሜሪካና በአውሮጳ ክፍለ ዓለማት የሚኖሩ እውነተኛ ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጆች በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች ለሆኑት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ የግፍ እስር የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት ቀጥለዋል። WASHINGTON, DC […]
የባልደራስ እጩ አባላት በወቅታዊ የምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አደረጉ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ለፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወከሉ እጩዎች በዛሬው እለት በራስ አምባ ሆቴል ፤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ የተለያዩ መርኃግብር እየተካሄደ ይገኛል ። የባልደራስ እጩ አባላት በወቅታዊ የምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አደረጉየዕለቱ መርኃግብር በግፉ ለተገደለው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል ዕጩ […]
ስለባልደራስ የእናቶች አስተያየት
እኔ-እናቴ ሰላም ዋሉማዘር-እግዚያብሄር ይመስገንእኔ- ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፖርቲ ዎች ነን ከተማችንን ለማዳን የእርስዎ ድምጽ ያስፈልገናል ካርድ አውጥተዋል ?!ማዘር- አዎ አውጥቻለሁ ልጄ ባልደራስ ማለት የዛ ጀግና የእስክንድር ነጋ ነው አይደል ?!እኔ-አዎ እናቴ !ማዘር-እንደው ምን አድርግ ነው የሚሉት?እኔ- እናቴ እውነትን ስለያዘ ይፈሩታል ፤ ከምርጫ ውጭ ለማድረግ ነው ። ሀሳብን ግን ማሰር አይችሉም የሱን ዓላማ ይዘን እስከመጨረሻው እንሄዳለን።ማዘር- […]
ባልደራስ በአዲስ አበባ ደረጃ የተቋቋመ የመጀመሪያው ‘ክልላዊ’ የፖለቲካ ፓርቲ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ቀኝ ዘመም (Center to right) ፓርቲም ነው። ባልደራስ ጥር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በሀቀኛው ጋዜጠኛ እና በፅኑው የሰብዓዊ መብቶች ታጋይ በአቶ እስክንድር ነጋ መሪነት በጎዳና ላይ ተመሰረተ። የግል ኩባንያ ከሆነው ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በዘጠና ሺህ ብር የተከራየውን የስብሰባ አዳራሽ በአምባገነኑ መንግሥት ተከልክሎ ጎዳና ላይ ቅድመ መሥራች […]
ወ/ሮ መሶበወርቅ ቅጣው፤ በባልደራስ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሕዝባዊ ውይይት ላይ ያደረጉት ንግግር
ክቡር አቶ አምሀ ዳኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ ክቡር ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ የተከበራችሁ እጅግ የምናከብራችሁ ደጋፊዎቻችን እና የፓርቲያችን አባላት በቅድሚያ በ6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የሚወዳደሩ የፓርላማ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት እጩዎቻችንን ለመተዋወቅና በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ጥሪያችንን አክብራችሁ በመምጣታችሁ በራሴና በባልደራስ […]
ባልደራስ ለአዲስ አባባ ባዘጋጀው ማኒፌስቶ ዙሪያ ከእጩዎች ጋር ምክክር አደረገ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ለፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት የተወከሉ እጩዎች ፤ለአዲስ አበባ በተዘጋጀው የምርጫ ማኔፌስቶ መርሐግብር ወይም አብይ ጉዳዮችን አፈፃፀም በተመለከተ ፤ውይይት እና ምክክር ።