ዜና(News)
ፍርድ ቤቱ መፍረድ አልቻለም !!
ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ ወይስ በድብቅ የሚለውን ፍርድ ለመስጠት ዛሬ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለወራት ጉዳዩን ይዞ ከቆየ በኋላ ” የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ግራና ቀኝ መርምሮ ውሳኔ ይስጥ ” በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል ።ትዕዛዝ የተሰጠው […]
ለሚዲያ አካላት የቀረበ ጥሪ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከዚህ ቀደም ሃገር አቀፍ የሆነውን ማኒፌስቶውን ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ነው፡፡በነገው ዕለት ግንቦት 3 ቀን 23/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በራዲሰን ብሎ ሆቴል በአዲስ አበባ ደረጃ የተዘጋጀው ማኒፌስቶ ይፋ የማድረግ እና የማስተዋወቅ ስነስርዓት ስለሚያካሄድ የድርጅታቹህ ሚዲያ ራዲሰን ብሉ ሆቴል በመገኘት የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡን ስንል በአክብሮት እየጋበዝን ለሚደረግልን ትብብር በቅድሚያ እናመሰግናለን ።ዝግጅቱ […]
ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ ነው
በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ 17 ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ በገፍ ለመጡ ወጣቶች በሕገ ወጥ ሂደት የመራጮች ካርድ እየታደለ መሆኑን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የምርጫ ጣቢያዎች የክትትል ቡድን አስታውቋል።ክስተቱን በምስል ለመቅረፅ የሞከሩት የባልደራስ የአካባቢው ተወካይ አቶ አንተነህ ደሳለኝ በፖሊስ ታስረዋል።ወጣቶቹ የመጡት ኮድ 3፡27401 ኦሮሚያ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ […]
ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ ወይስ በድብቅ የሚለውን ፍርድ ለመስጠት ለግንቦት 4 ተለዋዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ !
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ፤ በዛሬው እለት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ከቃሊቲ እስር ቤት ሆነው በፕላዝማ ቀርበዋል።ዛሬ በዋለው ችሎች ይጠበቅ የነበረው ፤ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ ወይስ በድብቅ የሚለውን ፍርድ ለመስጠት የተያዘ ቀጠሮ ነበር ፤ […]
እንኳን ለ80ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል አደረሠን !
ክብር ለአርበኞቻችን !!ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈቷ 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ደርጅታ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙሶሎኒ ትዕዛዝ ኢትዮጵያን ከሦስት አቅጣጫዎች ወረረች፡፡ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ የዘመተው የጣልያኑ ጦር አዛዥ ጄኔራል ባዶሊዩ አዲስ አበባ ገብቶ በታላቁ ቤተ መንግሥት የጣሊያንን ባንዲራ ሰቀለ። ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር […]
እነ እስክንድር ነጋ ለሚያዝያ 26 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው
የእነ እስክንድር ነጋን ዶሴ የተመለከተው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የፕላዝማ ችሎቱን አካሂዷል። በዚህም ምስክሮቹ በግልፅ ችሎት ይቅረቡ ወይስ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ካሉበት ወህኒ ቤት ሆነው በፕላዝማ ስክሪን ችሎት የቀረቡት የህሊና እስረኞች ምርጫው ሳምንት ሲቀረውም ቢሆን […]
የችሎት ውሎ
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በማገዱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለዛሬ የቀጠረውን የእነ እስክንድር ነጋን ችሎት ሳይዳኝ ቀረ፡፡ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በቀጠሯቸው መሠረት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ይሁን እንጂ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እያከራከረው በሚገኘው የይግባኝ […]
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ የላከው መልዕክት!
“ህዝቡ የምርጫ ሰራዊት መሆን አለበት። ይሄ ምርጫ የሚወስነው የአምስት ዓመት፣ የአስር ዓመትን ዕጣ ፋንታ አይደለም የትውልድን እንጂ።ስለዚህ ፣ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ፣ እንዲመርጥና ምርጫውን በታዛቢነት በንቃት እንዲከታተል ጥሪ አቀርባለሁ “ድል ለዲሞክራሲ