ዜና(News)
ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ሊመዘግብ ነው !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በወሰነው መሰረት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ በመጭው ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት እንዲቀርቡ ለማድረግ ሥራዎችን መጀመሩን አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የምርጫ […]
እነ እስክንድር በእጩነት እንዳይመዘገቡ የሚከለከሉበት ህጋዊ ምክንያት የለም !
በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እና በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ መካከል በተካሄደ ክርክር የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ፍርድ !! የእነ እስክንድር በእጩነት በተመለከተየፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ሰሚ ችሎት ፍርድ
እነ እስክንድር ነጋና ጠበቆቻቸው በሌሉበት ምስክሮችን እንዲሰማለት ዐቃቤ ሕግ ፍርድ ቤቱን ጠየቀ
ፍርድ ቤቱ ለሰኔ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷልበቃሊቲ ወህኒ ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) መሪዎች ማለትም እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። በባልደራስ የፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች […]
6ኛው ሃገራዊ ምርጫ እንዲታገድ ባልደራስ ፍርድ ቤትን ጠየቀ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች ፤ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ ፤በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር በዕጩነት እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።በውሳኔው መሰረት ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽም ባልደራስ በደብዳቤ የተጠየቀ […]
ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም አለ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ […]
የባልደራስ ፓርቲ አማራጭ የኢኮኖሚ ሞዴል
ዜጎች በተፈጥሮ እኩል በመሆናቸው የሰብዓዊ እንዲሁም የዜግነት መብታቸው መከበር አለበት፡፡ ተዘዋውሮ የመስራት፣ የመወሰን፣ ሀብት የማፍራት፣ በተገቢው ፍትሕ የመዳኘት እንዲሁም ንቁ ተሳትፎ የማድረግ እኩል ዕድል እና መብት አላቸው፡፡ በዘር፣ በቀለም፣ በሀብት፣ በጾታ፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት፣ ወዘተ. ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተገቢ አይደለም ብሎ ባልደራስ ያምናል። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ናት ሲልም በዚሁ የማያወላውል መርሑ እና ፅኑ እምነቱ […]
እነ እስክንድር ነጋ ለመጪው ምርጫ በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ የሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ
በቅድስት ሙላቱየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደመሌ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 16 በነበረው የችሎት ውሎው ነው።ችሎቱ ውሳኔውን የሰጠው የባልደራስ ፓርቲ አመራሮችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን እና በስተኋላ […]
እነ እስክንድር ነጋ ወደ ቂሊንጦ እንዲዘዋወሩ ቃሊቲ ወህኒ ቤት ጠየቀ
#በአስቴር ስዩም ላይ የድብደባ ሙከራ ተደርጓል#ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 17 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷልበቃሊቲ ወህኒ ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር (ቀለብ) ስዩም እና አስካለ ደምሌ ዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። በችሎቱም በኢትዮጵያ […]
ባልደራስ በአዲስ አበባ ደረጃ ያዘጋጀውን የምርጫ ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ !!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት በራዲሰን ብሉ ሆቴል “አዲስ አበባ ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋታለን ! ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ደራጃ የተዘጋጀውን ማኒፌስቶውን ይፋ አደረገ ።ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው ማኒፌስቶ 120 ገፆች ያሉትና በ2 ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው። የአዲስ አበባ ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶቿን በ19 ንዑስ ምዕራፎች በዝርዝር በማስቀመጥ ፤ ለእነኚህ […]