ዜና(News)
ባልደራስ አጣዮን መልሶ ለመገንባት የሚውል ድጋፍ አደረገ !
ባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አጣየ ከተማን መልሶ ለመገንባት የተያዘውን መርሃ ግብር የሚያግዝ የግንባታ ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል።ፓርቲው ለምርጫ ቅስቀሳ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የባነር መስቀያ ብረቶች እና እንጨቶችን መልሶ በመሰብሰብ ነው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገው።ድጋፉን ለመስጠት በአጣየ ከተማ የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሂምን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አባላት ተገኝተዋል።ባልደራስ ከዚህ ቀደም ከፖለቲካ ስራው ጎን ለጎን የተለያዮ […]
ባልደራስ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ መርሃ ግብሩን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ !
ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ጀምሮ በህዝባዊ እና በተሽከርካሪ ትዕይንቶች ታጅቦ በተለያዮ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የምረጡኝ የመዝጊያ ቅስቀሳውን አካሂዷል።በመርሃ ግብሩ ላይ የባልደራስ እና የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ፣ የፓርቲው የህዝብ እንደራሴ እና የክልል ም/ቤት ዕጩዎች፣የፓርቲዎች ደጋፊና አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎች ተገኝቷል።ፓርቲው ባካሂደው የመዝጊያ መርሃ ግብር ከተሳታፊዎቹ ባሻገር ከአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የነበረው አቀባባል ዕጅግ ከፍተኛ […]
በአፍራሾቿ ዶማ ላይ የተኛችው አዲስ አበባ (ጌጥዬ ያለው)
አንድ ተረት አለ፤ ትዝ የሚለኝ፡፡ ሁለት ወንዶች በአውድማ ተኝተው ነው፡፡ በውድቅት ሌሊት ጅብ መጣና የአንደኛውን እግር እንደሸንኮራ አገዳ ሞሽልቆ መቆርጠም ጀመረ፡፡ ጓደኛው ድምፅ ሰምቶ ምን እየሆነ እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ፈሪው ጓድ ‹‹ጅብ ነው፡፡ ተወው እግሬን ብቻ ነው የሚበላው›› አለው ነው ተረቱ፡፡ ‹‹ታዲያ እግርህን ከበላው ነፍስህንም እንዳይበላት ይሆን የምትጨነቀው?›› በማለት ጅቡን አባረረው፡፡ ፈሪውም አንካሳ ሆኖ ቀረ፡፡ በሰሞኑ […]
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆች የቀረበው አቤቱታ ላይ ፍ/ቤቱ፣ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።ጠበቆቹ በብይኑ ላይ ቅሬታ ስላደረብን ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን በማለት የህግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ […]
የሐዘን መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስክንድር ነጋ !
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት በተመለከተ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት የሐዘን መልዕክት ።”መካሪዬ፣ አባቴ፣ አስተማሪዬ የሆኑት በማረፋቸው በጣም አዝኛለሁ። ጓጉተውለት የነበረውን የዘንድሮ ምርጫ ውጤት አይተው ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃዱ አልሆነም። የሰላም እረፍት ይሁንላቸው። ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ”እስክንድር ነጋከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት
አስቻይ ሁኔታዎች በሌሉበት የሚከናወን ምርጫ ሀገር በጉጉት ወደምትጠብቀው ሥርዓት አያሸጋግርም !
በሕብር ኢትዮጵያ፣በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፣በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እናበእናት ፓርቲበጋራ የተሰጠ መግለጫሀገራችን ኢትዮጵያ የምታካሂደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ፍትህ፣ እውነተኛ ዲሞክራሲና ሠላም የራቀው ህዝባችንን አንድ እርምጃ ወደፊት በማራመድ በዚህ አቅጣጫ በምናደርገው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ከፋች እንደሚሆን በማመን በምርጫው ሂደት ከመነሻው ጀምሮ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡በታሪኳ ተዓማኒነት ያለው ምርጫ አካሂዳ ለማታውቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ምርጫው […]
ለ1997 ዓ.ም. ሰማዕታት ቋሚ መታሰቢያ ይቁምላቸው!
ያለፈው ይብቃ!ለ1997 ዓ.ም. ሰማዕታት ቋሚ መታሰቢያ ይቁምላቸው!ባለፈው አመት ልክ በዛሬዋ ቀን የዚህን ተመሳሳይ መግለጫ አውጥተናል። ዛሬም እንደግመዋለን፤ የ1997 ምርጫ ሰማዕታትን ሁልጊዜም ስናስታውሳቸው እንኖራን። እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም ቋሚ መታሰቢያ እንደመቆምላቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ይጠይቃል።1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያውያን ዘንድ በዘመናት መካከል የማይረሳ ጊዜ ነበር፡፡ እልፎች ኢትዮጵያውያን የንጋት ምልክት ያዩ መስሏቸው ለምርጫ የወጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሁን […]
በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሴት ዕጩዎች ብቻ የተመራ የምርጫ ቅስቀሳ !
” አዲስ አበባን ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋታለን !”ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የባልደራስ-ሴት-አባላት-ቅስቀሳ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች ፤ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ የዕጩነት የማረጋገጫ ሰንድ !