ዜና(News)
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ለነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ‘የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባና በዝግ ችሎት ይቅረቡ ወይስ በግልፅ ችሎት ይሰሙ’ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ነው። ትናንት ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበረው ችሎት መዝገቡን አለመመርመሩን ጠቅሶ ለዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ማሸጋገሩ ይታወሳል።ይህንኑ የምስክሮች አሰማም ሂደት በተመለከተ […]
ለባልደራስ ክስ ምርጫ ቦርድ ነገ በፍርድ ቤት መልስ ያቀርባል !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ምርጫ 2013 ላይ የተሠሩ ሕገ ወጥ ተግባራትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅሬታዎችን ቢያቀርብም ከሕግ አግባብ ውጭ በማን አለብኝነት ውድቅ ተደርገውበታል። በመሆኑም ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶ በምርጫ ቦርድ ላይ ሕጋዊ ክስ መስርቷል።ፓርቲው ለመሰረተው ሕጋዊ ክስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነገ ሀምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ […]
አስቸኳይ ማስተካከያ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የ2013 ዓ.ም. ምርጫን አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በራስ አምባ ሆቴል ረፋድ 4፡00 ሰዓት ይፋ ለማድረግ ለመገናኛ ብዙኅን ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።ይሁን እንጂ ባልደራስ ሊሰጠዉ ያቀደው ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግስት አፋኝ ቡድን በመከልከሉ ጥናቱን በተጣበበ ቦታም ቢሆን በቢሯችን ይፋ ለማድረግ ወስነናል።በመሆኑም በተጠቀሰው ሰዓት ስድስት ኪሎ፤ ምስካየኅዙናን መድሀኒያለም […]
የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ
የሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን ምርጫ በተመለከተ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አጠቃላይ ውጤት መገለጹ የሚታወቅ ነው።ይህም በመሆኑ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የ2013ን ምርጫ አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በራሳ አምባ ሆቴል ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይፋ ያደርጋል ። የእለቱን መርሃግብር የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ ስንል ጥሪ እናቀርባለን ።ከሠላምታ ጋር !
ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ለሃምሌ 29 እነ እስክንድርን በድጋሜ ቀጠረ
አቃቤ ሕግ ከጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ያወጣውን የዕግድ ትዕዛዝ ማህተም አስደርጎ ለ9 ሰዓት “ቀርቢያለሁ” ማለቱን ተከትሎ ነው በድጋሜ ለሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም የተቀጠረው።የፌደራሉ ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ባወጣው የዕግድ ትዕዛዝ ዙሪያ ሐምሌ 26 /2013 ዓ.ም የግራ ቀኙን ጉዳይ ለመመልከት ቀጠሮ ሰጥቷል።ከፍተኛ ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት በአምስት ቀናት ውስጥ ምስክር እንዲያሰማ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል። […]
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ !
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442 ኛው የኢድ አል- አዷኻ/አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ምርጫ ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (#ባልደራስ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ባልደራስን ወክለው በምርጫ ጣቢያዎች ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ ።በመርሃግብሩ ላይ የባልደራስ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን በምርጫ 2013 አስተዋፅኦ ያደረጉ ታዛቢዎችንያመሰገኑ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ጊዜያትም በተጠናከረ መልኩ ከባልደራስ ፓርቲ ጋር በአጋርነት አብረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የምስጋና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው […]
ዐቃቤ ህግ ዛሬም ምስክሮቹን በችሎት ፊት ማቅረብ አልቻለም!
ከዛሬ ጀምሮ ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማሰማት እንዲጀምር የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማቅረብ አልቻለም ። ምስክሮቻችንን በ15 እና 16 እናሰማለን እስከዚያ ድረስም ለምስክሮች ጥበቃ የሚያስፈልጉ ተግባራትን አከናውናለው በማለት ዐቃቤ ምስክሮቹን አለማቅረቡን ለፍ/ቤት ተናግሯል ።ይሁን እንጂ የግፍ እስረኞች ጠበቆች ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ውድቅ በማድረግ ። ምስክር አሰማሙ በአምስት […]
በነ እስክክንድር መዝገብ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት በዐቃቤ ህግ ምክንያት ቀረ !
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል።ከዚህ ቀደም በዋለው ችሎት ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት […]