ዜና(News)
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ60 በላይ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ለቤተመንግስት ማስፋፊያ በሚል በመንግስት ሀይሎች መፍረሳቸው ተነገረ
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ብሎክ አንድ ፤ሶስት እና አራት የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታችን በሕግ ወጥ መንገድ በመንግስት ሀይሎች ፈርሶብናል ብለዋል፡፡ የቀጠና አንድ ቁልቢ ኮሚቴ አመራሮች እንደተናገሩት ከሆነ ከ60 እስከ 65 የሚደርሱ ቤቶች በቀን 17 2/2015 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች ከጠዋቱ 11፡30 ጀምሮ በኃይል ፈርሰዋል ፡፡ ቤቶቹ የፈረሱት አዲስ ይገነባል በተባለው የቤተ-መንግስት ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው […]
የባልደራስ ድጋፍ ሰጪ በሰሜን አሜሪካ
በእስክንድር ላይ የተፈጸመው ጥቃት ፤የፍትሕ ሥርዓቱ ዝቅጠት ማሳያ ነው !!!
ህመሙ _አመመኝ
አቶ ስንታየሁ ቸኮል የኅሊና እስረኛ ከቂሊንጦእስክንድር ነጋ የድርጅቴ መሪ ራስ ነው! ለኔ ደግሞ የሥራ አለቃዬ ነው!እስክንድር ታላቅ ወንድሜ መካሪዬ ነው። እስክንድር ለጋራ መስዋዕትነት የተጠራን የቁርጥ ቀን የሀገሬ ሕብረ_ቀለም ሃቀኛ ጓዴ ነው።ከመሪዬ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን በተቀራረበ መኝታ ላይ እንዴት እንዳዳረ አውቃለሁ። ህመሙ- አመመኝ… ላብ በሚያጠምቅ ምጥ ..እእእእእ… የጥዝጣዜ ስሜት ቦታው ላይ መፍትሄ አጥተህ መጋራት […]
የእስክንድር እግር መሰበሩ በህክምና ተረጋገጠ !
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዕቅድ የተደበደበው እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ሆስፒታል በተደረገለት ህክምና ፣ በግራ እግሩ ላይ ያለው አውራ ጣቱ መሰበሩ በራጂ ተረጋግጧል።በዚህም መሠረት፣ ለሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታት የሚቆይ ጄሶ ተደርጎለታል።እስክንድር ከማረሚያ ቤት ሆኖ ባስተላለፈው መልዕክት፣ “በሰሜን ያለውን ጦርነት አስባለሁ። የታሰሩትን አባሎቻችንን አስባለሁ። አጥንታችንን መስበር ይቻላል። ትግላችንን ግን መስበር አይቻልም […]
በጅምላ ከታሰሩት መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጠሩ !
የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 ዓ/ም የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ ታፍሰው መታሰራቸው ይታወቃል።አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት የሰሙ ታዳሚዎች እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው የወጡ ሲሆን ፤ ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ […]
በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን!!!
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር አብረው በእስር ላይ ያሉት የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተገኙ ሲሆን የባልደራስ […]
መረጃ ! በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል
በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል ። በዚህም ምክንያት ጉልበቱ መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ የተባሉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል! በዛሬው ዕለት እስክንድር ነጋ ችሎት መቅረብ አልቻለም ።ይህም በመሆኑ በተከታታይ ምስክር የመስማት ቀጠሮ ተሰርዞ ፤ ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ተዘዋውሯል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ችሎት ለመታደም የተገኙ በጅምላ ታፍሰው […]
ነገም እንደዛሬው የሞራል ግዴታችንን እንወጣ!
በዛሬው የእነ እስክንድር ነጋ ችሎት ላይ ለመታደም የፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ መጥታችሁ ‘አዳራሽ ሞልቷል’ በሚል ችሎቱን ሳትታደሙ የተመለሳችሁ የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ተቆርቋሪዎች በርካቶች ናችሁ። ከኅሊና እስረኞች ጎን መሆናችሁን ስላሳያችሁን በእጅጉ እናመሰግናለን።ችሎቱን የታደማችሁም ሆነ የተከለከላችሁ አጋርነታችሁን አሳይታቸሰኋልና ፈጣሪ አጋር ይሁናችሁ። የሞራል ግዴታችሁን መወጣታችሁ በታሪክ ተመዝግቦ ለትውልድ እንደሚተላለፍም ተስፋ እናደርጋለን።ችሎቱ ነገም ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. […]
ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድ ነጋ ላይ የሚቀርቡ ምስክሮች ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ ያቀረበውን አቤቱታ ፍ/ቤት ውድቅ አድርጎታል
በዚህም መሰረት ፦በነ #እስክንድር ነጋ ላይ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ዐቃቤ ሕግ የዘረዘራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር:-1. ፈንታሁን አሰፋ2. መንበረ በቀለ3. ወርቁ ታደሰ4. ፍፁም ተሰማ5. ደረጀ ግዛው6. ቴዎድሮስ ለማ7. ያየህ ብርሃኑ8.ጌትነት ተስፋዬ9. ትንሳኤ ማሞቀሪ የ12 ምስክሮች ስም ዝርዝር ነገ ጧት እንዲቀርብ ታዝዟል። ከላይ ከተጠቀሱት መካከል ሁለቱ ነገ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ […]