ዜና(News)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች የምስራቅ ወለጋ አጎራባች በሆነው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ ታህሳስ 01/2015 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የሰባቱን ሟቾች አስከሬን ብቻ መቅበር ተችሏል፡፡ በሀይል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡት የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የተገደሉ ህፃናት፣ሴቶችና አዛውንቶች አስከሬን በየጫካው ወድቆ […]
የባልደራስ ፓርቲው አቶ ካሳሁን ደስታ በፖሊስ ታገቱ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ንቁ አባል እና ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ዛሬ ጠዋት፤ በትላንትናው ዕለት 03/04/2015 ዓ.ም ለታሰሩት አቶ ናትናኤል ስንቅ ለማቀበል ሄደው ነበር። ሆኖም በሄዱበት ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ (ላዛሪስት ፔኒሲዮን) የሚገኘው የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በዛው አግቶ አስቀርቷቸዋል።አቶ ካሳሁን ፓርቲያቸውን እና ሀገራቸውን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ ሰላማዊ-ታጋይ ናቸው።
አቶ ናትናኤል የአለምዘውድ ታሰሩ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ንቁ አባል የነበሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ባልታወቁ ደህንነቶች ዛሬ በሰፈራቸው ቀጨኔ መድሃኒአለም አካባቢ ተይዘዋል።አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ቀድሞው ህወሃት መራሹ መንግስትም ሆነ በአሁኑ የኦሮሞ-ብልፅግና መራሹ መንግስት በተደጋጋሚ ታስረዋል።
በወቅታዊ የፓርቲያችን እንዲሁም የሀገራችን ሁኔታ ላይ የተደረገ ውይይት
የባልደራስ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት ዶ/ር በቃሉ አጥናፉና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በወቅታዊ የፓርቲያችን እንዲሁም የሀገራችን ሁኔታ ላይ ተወያይተወዋል። ውይይቱን ከታች ባለው ሊንክ (Link) በመግባት ይከታተሉ።ሊንኩን ለመክፈት እዚህ ይጫኑ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያካሂድ ውሳኔ ተላለፈ
በቀን 20/03/2015 ዓ.ም በቁጥር አ1162/11/782 በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው ሊያደርግ ያቀደው ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ እንዲችል በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አይቶ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም የፓርቲው ም/ፕሬዚዳንት አቶ አመሃ ዳኜው ምክትል ፕሬዚዳንትነት በፓርቲው ህገ ደንብ መሰረት የተከናወነ መሆኑን በማረጋገጡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የምትገኙ አባላትና ደጋፊዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ […]
ኦነግ ሸኔ በከፈተው ጦርነት ምክንያት የአ.አ- ጎጃም መስመር ተዘጋ
“መንግስት ካለ መረጃውን ለህዝብም ለመንግስትም አድርሱልን”። ይህ መልእክት ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሲጓዙ የነበሩ ተሳፋሪዎችና ሹፌሮች ያስተላለፉት መልክት ነዉ። በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ጎጃም መስመር ሲጓዙ የነበሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች፣የጭነት መኪኖች፣እስክሬን የጫኑ መኪኖች፣ የግለሰብ መኪኖች እንዲሁም አገር አቋራጭ ነዳጅ እና ሸቀጣሸቀጥ የጫኑ መኪኖች በሙሉ አሊ ዶሮ አካባቢ ኦነግ ሸኔ በከፈተው ከፍተኛ ጦርነት አማካኝነት መንገድ […]
ለቤተመንግስት መስሪያ ሲባል ዜጎች ተፈናቅለው ወደ ጎዳና ሊወጡ ነው
ከወር በፊት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እየተሠራ ነው በሚባለው ቤተ-መንግሥት ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅያሪ ቦታ ቤት መቀለሻ ገንዘብ ሳይሰጣቸው በላያቸው ላይ ሊፈርስ እንደሆነ ከነዋሪዎቹ በደረሰን ጥቆማ መሠረት አቤቱታቸው ሰሚ ያገኛል በሚል ተስፋ ፓርቲያችን ባልደራስ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ በወቅቱ ቤቶቹን በነዋሪዎቹ ላይ የማፍረስ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን ተገትቶ ነበር፡፡ ይሁንና አሁንም የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ነዋሪዎች ምንም […]
የሃዘን መግለጫ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአሜሪካን የባልደራስ ደጋፊ የነበሩትን ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ወዬሳን ድንገተኛ ሞት ሲሰማ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶታል። አቶ ዳዊት ከበደ በጋዜጠኝነት ሙያ ለረጅም ጊዜ ሀገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ከመሆኑም ባሻገር ሙያቸውን አክባሪ፣ ትሁትና ቅን ሰው ወዳድ እንደነበሩ የሚታወቅ ነው። ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የፓርቲያችን መሥራችና ፕሬዚዳንት ከነበሩት ከጀግናው እስክንድር ነጋ ጋር የነበራቸው ሙያዊ […]
በባልደራስ ስም ሃክ በተደረጉ የፌስቡክ አካውንቶች የሃሰት መረጃ የሚያሰራጩ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የባልደራስ ሥ/አስፈጻሚ አስጠነቀቀ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚይዘው አቋም የሚገለፀው፡- 1. በራሱ የተረጋገጠ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ 2. በጽ/ቤቱ በኩል የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች በሚላኩ አቋም መግለጫዎች ነው፡፡ ከእነዚህ ውጭ በማናቸውም ሁኔታ የሚወጡ ፅሁፎች ባልደራስን አይወክልም፡፡ በመሆኑም የጥቅምት 21/15 ዓ.ም “ጌጥዬ ያለው” በሚል ሀክ በተደረገ የፌስቡክ ገፅ ላይ የፓርቲያችን አቋም ያልሆነ ባለ 4 ገፅ […]