ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ለሃምሌ 29 እነ እስክንድርን በድጋሜ ቀጠረ
አቃቤ ሕግ ከጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ያወጣውን የዕግድ ትዕዛዝ ማህተም አስደርጎ ለ9 ሰዓት “ቀርቢያለሁ” ማለቱን ተከትሎ ነው በድጋሜ ለሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም የተቀጠረው።
የፌደራሉ ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ባወጣው የዕግድ ትዕዛዝ ዙሪያ ሐምሌ 26 /2013 ዓ.ም የግራ ቀኙን ጉዳይ ለመመልከት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ከፍተኛ ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት በአምስት ቀናት ውስጥ ምስክር እንዲያሰማ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል። ይሁን እንጅ ሁለቱን ቀናት ምስክሮችን ሳያቀርብ ቆይቶ በሦስተኛው ቀን ላይ የዕግድ ትዕዛዝ ዛሬ አምጥቷል።
የተከሳሽ ጠበቆች “አቃቤ ሕግ የዕግድ ትዕዛዝ ከጠቅላይ ሰበር ቢያመጣም እነ እስክንድርን አስሮ ማቆየት የሚያስችል አንዳች የህግ ምክንያት የለም፤በመሆኑም በአካልና በህሊና ነፃ ሊወጡ ይገባል፤ጠቅላይ ሰበርም ቢሆን ስለ ቀጣይ አያያዛቸው ያቀረበው ትዕዛዝ የለም ፤ በመሆኑም የወንጀል መቅጫ ስነ ስርዓት ህግ 94 ታይቶ ደንበኞቻችን ነፃ ሊባሉ ይገባል” በሚል ተከራክሯል።ይሁን እንጅ ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ሳይቀበል ቀርቷል።
ይህንን ተከትሎ አቃቤ ህግ ሆን ብሎ የፖለቲካ ትዕዛዝ በመቀበል የነ እስክንድርን በአካልና በህሊና ነፃ የመውጣት ሂደት እያስተጓጎለ መሆኑ ከፍተኛ ብስጭት ፈጥሯል።
ዛሬም እንደተለመደው በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባ ኗዋሪ ተገኝቶ ለነ እስክንድር ያለውን ድጋፍ አሳይቷል።
“የዘገየ ፍትህ እንደሞተ ይቆጠራል።”
ሃምሌ 2013
ወግደረስ ጤናው