ከባልደራስ ፓርቲ ታሪካዊ ቀናት በጥቂቱ

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ)፦ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በባልደራስ አዳራሽ ተመሠረተ።
በይፋ ወደ ፓርቲነት እንዲያድግ ከህዝብ ጥያቄ ፦ በሕዳር 15/2012 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ቀረበ።
የቅድመ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤውን ፦ ጥር 3/ 2012 ዓ.ም ካዛንቺስ ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ (መንገድ ላይ) አደረገ።
የፓርቲውን ስያሜው “ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ” ብሎ በመሰየም ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱ አድርጎ መረጠ።
የፓለቲካ ፓርቲ የጊዜያዊ የምዝገባ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፦ ጥር 4/2012 ዓ.ም ተቀበለ።
የመስራች ጉባኤውን፦ የካቲት 1/2012 ዓ.ም በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ አካኼደ።
ፕሬዝዳንቱን እስክንድር ነጋን ጨምሮ አመራሮቹ ፦ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም ከዋናው ፅ/ቤት እና ከሌሎች አካባቢዎች ተወስደው ታሰሩ።
ከአመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ መሪዎቹ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ አመራሮቹ ፦ ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም ተፈቱ።
ከ25 በላይ አባላቶች እና አመራሮች የካራማራን ድል ሊያክብሩ በሄዱበት በአገዛዙ ፦ የካቲት 26/2014 ዓ.ም ድላችን ሀውልት፣ ጥቁር አንበሳ አካባቢ ተይዘው ታሰሩ።
የሀገር አቀፍ ፊርማ ማሰባሰብ ማስጀመሪያ ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት በአርባ ምንጭ ተካሄደ፦ ሚያዝያ 12/2014 ዓ.ም።
ወደ አርባምንጭ የሄደው በፕሬዝዳንቱ የተመራው ልኡክ ቡድን ታስሮ በማግስቱ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለስ ፦ ሚያዝያ 12 እና 13 /2014 ዓ.ም ተደረገ።
መሪው እስክንድር ነጋ ለቤተሰብ ጥየቃ እና ለፓርቲ ስራ ወደ አሜሪካ፦ ሚያዝያ 15/2014 ዓ.ም ሄዱ።
ከወራት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ አቶ እስክንድር ነጋ ወደ ሀገር ፦ ሐምሌ 6/2014 ዓ.ም ተመለሱ።
ፕሬዝዳንቱ እስክንድር ነጋ በፃፉት ደብዳቤ ምክንያቶቻቸውን ጠቅሰው ከአመራርነትም ሆነ ከአባልነት ከፓርቲው መልቀቃቸውን ፦ ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም አሳወቁ።
በወቅቱ ም/ፕሬዝዳንት ኋላ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አምሃ ዳኜው ጉባኤ ለማካሄድ በስራ ላይ እያሉ በአገዛዙ ፦ መጋቢት 2/2015 ዓ.ም ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ተወስደው ለሰአታት ታገቱ።
ከብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎች/ፈተናዎች በኋላ የአንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማድረግ:- መጋቢት 3/2015 ዓ.ም በጋምቤላ ሆቴል ቢሰበሰብም በአገዛዙ አፈና ምክንያት ጉባኤው ሳይደረግ ቀረ።
ፓርቲው ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ “አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን” ፦ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሆቴል በማካኼድ አቶ አመሃ ዳኜውን በፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የምክርቤት፣ የኦዲትና ቁጥጥር እና የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባላትን መረጠ።
ፓርቲው ወደ ሀገር አቀፍነት እንዲያድግ እና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ እንዲሰራ ጠቅላላ ጉባኤው ፦ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ወሰነ።
ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት ለማደግ የፊርማ ማሰባሰብ ስራ ፦ የካቲት 24/2016 ዓ.ም ጀመረ።
ከአራት ክልሎች 6 ሺህ ፊርማ ብቻ ቢጠበቅበትም፣ ከስድስት ክልሎች አስር ሺህ ፊርማ በማሰባሰብ ለምርጫ ቦርድ ፦ ግንቦት 19/2016 ዓ.ም አስገባ።
የሀገር አቀፍ ፓርቲነት የምስክር ወረቀቱን ፦ ነሐሴ 23/2016 ዓ.ም ተቀበለ።
ድል ለኢትዮጵያ!
ድል ለዲሞክራሲ!