ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነታችን የት ነው?
(ጌንመ ዘብሔረ አዲስ አበባ )
ዛሬ በውስጤ ስለሚብሰለሰለው የኦሮሞ ማንነት ጉዳይ እንነጋገራለን:: ሀሳቡን ከእኔ የተሻሉት ደግሞ አዳብረው ቢያቀርቡት ትልቅ ትርፍ ይኖረዋል ብዬ አምንለሁ::
ኦሮሞነት በሁለት ይከፈላል:: እነርሱም ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትና ባንዳዊ ኦሮሞነት ነው:: ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነት ሀገር በቀል የሆነ ጥርት ያለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ባንዳዊ ኦሮሞነት ደግሞ መነሻውን ኢትዮጵያን ሊያፈርሷት ከሚፈልጉት ከነ ግብፅ ፣ ጣሊያን ፣ አረቦችና አውሮፓዎች ያደርጋል::
እነዚህን ማንነቶች በሰው ማንነት መግለፅ ቢፈለግ፡-
- ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነት በጀግናው አርበኛ ጣሊያንን ባርበደበደው ሥመ ጥሩው ጀነራል ጃገማ ኬሎ ይመሰላል::
- ባንዳዊ ኦሮሞነት ደግሞ በጎጠኛ ባንዳው ከሱማሌ እና ከወያኔ ጋር ባደረው የውጭ ጠላት ተላላኪው በዋቆ ጉቱ ይመሰላል::
እነዚህ ሁለቱም ኦሮሞነቶች የየራሳቸው መገለጫዎች ሲኖራቸው በዝርዝር ብዙ ማንሳት ቢቻልም ለዚህች ትንሽ ጽሑፍ ውስን ሀሳቦች ብቻ ላንሳ:: ለምሳሌ የኢትዮጵያዊ ኦሮሞነት መገለጫው በሀገሩ ጉዳይ አለመደራደር ፣ ለባንዲራውና ለሀገሩ ቀናዪ መሆን ፣ ታማኝ፣ ሀቀኛ ፣ ወገኑን እጅግ የሚወድና ከኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ጋር በጋብቻም ይሁን በዝምድና መተሳሰርን የሚወድ ፣ ለወገኑ የሚሞት ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ የባንዳዊ ኦሮሞነት መገለጫው ከጠላት ጋር የሚተባበር፣ ገንዘብ ወዳጅ፣ ኢትዮጵያንና ባንዲራዋን የሚጠላ፣ የበታችነት ስሜት ያለበት፣ ቂመኛ፣ በቀለኛ፣ ዘራፊ፣ ሁሉ ለእኔ ብቻ የሚል፣ ወገን ጠል የሆነ፣ ሀገር ቢበተን ምንም የማይመስለው፣ የሚጠላ፣ የበላይ ሆኖ መኖር የሚመኝ እና ሁሉንም መሰልቀጥ የሚፈልግ ነው::
አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የኦህዴድ ብልፅግና/ ኦሮሙማ/ እና ኦነግ ከሁለቱ የኦሮሞነት መገለጫ ተነስተን ስንመዝነው የባንዳዊ ኦሮሞነት ባህሪ ውስጥ ሆነው እናገኛቸዋለን::
በዚህ ጽሑፍ ማንሳት የፈለኩት ከባንዳዊው ኦሮሞነት ባህሪ ውስጥ ሁሉን የመሰልቀጥ አባዜው መሃከል ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትን ለመሰልቀጥ እየሄደበት ያለበት መንገድን ነው::
በጣም የሚገርመው የባንዳዊው ኦሮሞነት የመሰልቀጥ አባዜ ምንም ሀፍረት ሳይሰማው ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትን በኦሮሞ ስም አንድ ነን በሚል የተምታታ የሀሰት ትርክት ለመሰልቀጥ እየሄደ ያለበት ርቀት ነው:: በምን መንገድ ይሆን ዘይት እና ውሃ የሚቀላቀለው ?
በምንስ መንገድ ይሆን ጀግናው በአርበኛው ጀነራል ጃገማ ኬሎ ከባንዳዊ ዋቆ ጉቱ ጋር የሚቀላቀለው? ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትን ለራሱ መሰልቀጥ የሚፈልገው ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወቱትን ኦሮሞዎችን ሥማቸውን ብቻ በመውሰድ እነርሱ ለሚፈልጉት የፖለቲካ ቁማር አካል ሊያደርጋቸው ሲሞክሩ እና የልጅ ልጆቻቸውን ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎችን ሊያምታቱበት ሲሞክሩ ይስተዋላል:: ይህም ማለት ለኢትዮጵያዊ ኦሮሞነቱ እነርሱ በሚፈልጉት የባንዳዊ ኦሮሞነት ጠባብ ልብስ አሰፍተው ሊያለብሱት ሲሞከሩ ይታያል::
ለምሳሌ፡- በዘንድሮው በ125ኛው የአድዋ በዓልን የጀግናውን የአርበኛውን የሥመ ጥሩውን የደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ ፎቶ ለጥፎ በክልል ደረጃ በሚል የልጆች ብልጣብልጥነት አ/አ ላይ አክብረውታል:: ይህንን ሲያደርጉ ዓላማቸው አርበኛው አባታችን ከተሰለፈለት ዓላማ በተቃራኒው በሆነ ታሪክ በራሳቸው የባንዳነት ዓላማ ባለው ልብስ አሰፍተው ሲያለብሱት አስተውለናል:: ለሀገሩ ለእምዬ ኢትዮጵያ የተጋደለውን “ ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ ፤ መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ “ ተብሎ የተገጠመለትን ሀገር አቀፉን ጀግና የኦሮሞነት ስብዕና ብቻ በማልበስ በኦሮሞነቱ ነው ድል ያደረገው በሚል መንፈስ የተዛባ ታሪክ ለመፍጠር ሲውተረተሩ ይታያል::
ጀግናው አርበኛው ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በጣሊያን ወራሪ ሲወረር ዘራፍ ብሎ ሄዶ የተዋጋ እና ድልም ያደረገ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ነው:: ነገር ግን ኦነጋዊው የኦሮሙማው ብልፅግና የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በሱዳን ተወርሮ እያየ ሀገረ መንግስቱን ይዞ የናንተ ችግር የኔ ጉዳይ አይደለም ብሎ ይህው ቁጭ ብሎ ይመለከታል:: የነገ የታሪክ ተወቃሽነት ከቶ አያስጨንቃቸውም:: ሀገርን ለማስተዳደር ቦታ ይዞ ከመንደሩና ከጥቅሙ በላይ ማሰብ አይችልም:: ይሄ ነው እንግዲህ ባንዳዊ ኦሮሞነት ማለት ለሀገር የማይጠቅም ድኩማንነት::
በሌላ በኩል ደግሞ ጣሊያንን ያርበደበደዉን የሀገር እና የአፍሪካ ኩራት የሆነውን የሥመ ጥሩውን የጀግናውን እና የአርበኛውን የጀነራል ጃገማ ኬሎን ሥም ከቶ ማንሳት አይፈልጉም፤ ሥራውንም መዘከር ደግሞ እጅግ በጣም የሚፈሩት ጉዳይ ነው:: ጀነራል ጃገማ ኬሎ ስለ ኢትዮጵያ አውርቶ የማይጠግብ ባንዲራዋን ለብሶ ውሎ ለብሶ ቢያድር የሚወድ፣ ስለ ሀገሩ የሚቆጭ፣ ስለ ወገኑ የሚቆረቆር፣ ትዉልዱን ሀገራችሁን ውደዱ ጠብቁት ለእርሷም መስዋዕት መሆን ካለባችሁ መስዋዕት ሁኑላት ብሎ የሚመክር ፣ ሆኖም ያሳየ፣ ስለ ኢትዮጵያ ሀገሩ የሚዘምር ታላቅ አባት ሆኖ ሳለ ስለ እርሱ አንድ ነገር ማንሳት የሞት ሞት ነው የሚሆንባቸው::
በተቃራኒው ባንዳዊ ኦሮሞው ዋቆ ጉቱ ደግሞ ከጠላቶቻችን ከወራሪው የሱማሌው ዚያድባሬ ጦር ጋር በማበር በባሌ በኩል ሀገርን እያስመታ እና ጦር አደራጅቶ ወገንን እያስጨረሰ ብዙ መከራ ፈፅሟል:: ዐላማውም የባንዳዎች ሀሳብ የሆነውን ኢትዮጵያን የመበታተን እና የማፈራረስ ህልም ተፈፃሚ በማድረግ ኦሮሞን ከተቀረው የኢትዮጵያ ወንድሞቹና እህቶቹ መነጠል ነበር:: ኢትዮጵያንም ለማዳከም በ1950ዎቹ በሱማሊያ ውስጥ ስልጠና የወሰደ፣ ከወያኔ ጋር አብሮ ይሠራ የነበረ እና የመጀመሪያ የኦነግን ባንዲራ በባሌ ጫካ ውስጥ ያውለበለበ እርጉም የባንዳዊ ኦሮሞነት ተምሳሌት ነበር:: በኋላም በጀግናው ጀነራል ጃገማ ኬሎ የተማረከ መሆኑ ይታወሳል::
ነገር ግን ለዚህ ሰው ሀዉልት አቁመዉለታል፣ በስሙ ት/ቤት ፣ ባንክ እየሰየሙ ትልቅ ጀብድ እንደሠራ ሲክቡት ይስተዋላል:: አሁን በሥልጣን ላይ ባለው የኦሮሙማ መራሹ መንግሥት እየሆነ ያለው ግብፆች ፣ አረቦችና ነጮች እንደ እቅድ የያዙትን ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትን እና ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፋትን እና ባንዳዊ ኦሮሞነትን በኦሮሚያ ምድር በማንገስ የኢትዮጵያን ታሪክ አበላሽቶ ሀገርን መበታተን ነው:: እንደ ዋና ዓላማ አድርገው እየተንቀሳቀሱበት ያለው ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎች የተሰውለትን እና የሞቱለትን ዓላማ በማዳከም ታሪክ የሠሩትን ሰዎች ሥም እና ዝና ብቻ በመውሰድ እነርሱ በሚፈልጉት የባንዳነት ልኬት መስፋት ሲሆን ሀገር ብለው ከደቡብ ሰሜን ከምዕራብ ምሥራቅ በእግር ተጉዘዉ ሀገር ለመታደግ የተጠቀሙበትን ዓላማና ፍቅር ሳያነሱ ስማቸውን ብቻ በመውረስ ተግባራቸውን መሰልቀጥ ነው::
ሌላኛዉ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሀገር ወዳድ አርበኛ ኦሮሞዎችና ቤተሰቦቻቸውን በማሸማቀቅ የመሰልቀጥ ፖሊሲያቸውን እያራመዱበት ያሉት መንገድ ስንመረምር ዛሬና ነገ ተከታይ አርበኛ ትውልድ እንዳይተካ የወጠኑት የዱኩማን አስተሳሰባቸው አካል መኾኑን እንረዳለን::
ስለዚህ እናንት ጊዜ የሰጣችሁ የወያኔ ምትክ የሆናችሁ የረከሰ ኦነጋዊና ኦህዴዳዊ ብልፅግና የጎሳ ፖለቲካ ቁማርተኞች፤ ንብረት፣ ቁሳቁስና ባንኮችን እንደምትዘርፉት ሁሉ የኢትዮጵያዊ ኦሮሞነትንም ከእምዬ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ለማጥፋት እየሠራችኹ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተገንዝቦታል:: እየዘረፋችሁ ያላችሁትን ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነታችንን ብትመልሱልን ይመረጣል::
ከዚህ በኋላ እኛ ኩሩ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎች ትግላችን ከነ ደጃዝማች ባልቻ አባነብሶ ከነ ጀነራል ጃገማ ኬሎ ከአያት ቅድም አያቶቻችን የወረስነውን ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነታችንን ማስመለስና ማስጠበቅ እንዲኹም እምዬ ኢትዮጵያ ሀገራችንን በጋራ ማቆም ይኾናል!!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!!!