አስቸኳይ ማስተካከያ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የ2013 ዓ.ም. ምርጫን አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በራስ አምባ ሆቴል ረፋድ 4፡00 ሰዓት ይፋ ለማድረግ ለመገናኛ ብዙኅን ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ባልደራስ ሊሰጠዉ ያቀደው ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግስት አፋኝ ቡድን በመከልከሉ ጥናቱን በተጣበበ ቦታም ቢሆን በቢሯችን ይፋ ለማድረግ ወስነናል።
በመሆኑም በተጠቀሰው ሰዓት ስድስት ኪሎ፤ ምስካየኅዙናን መድሀኒያለም አጠገብ በሚገኘው ዋናው ቢሯችን በመገኘት እንድትዘግቡ ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ከሠላምታ ጋር !