ባልደራስ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ መርሃ ግብሩን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ !
ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ጀምሮ በህዝባዊ እና በተሽከርካሪ ትዕይንቶች ታጅቦ በተለያዮ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የምረጡኝ የመዝጊያ ቅስቀሳውን አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የባልደራስ እና የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ፣ የፓርቲው የህዝብ እንደራሴ እና የክልል ም/ቤት ዕጩዎች፣የፓርቲዎች ደጋፊና አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎች ተገኝቷል።
ፓርቲው ባካሂደው የመዝጊያ መርሃ ግብር ከተሳታፊዎቹ ባሻገር ከአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የነበረው አቀባባል ዕጅግ ከፍተኛ ነበር።
በግፍ በዕስር ላይ የሚገኙትን የፓርቲውን ፕሬዝዳንት እና የየካ ክፍለ ከተማ ዕጩ የሆነውን እስክንድር ነጋን ጨምሮ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣አስካለ ደምሌ እና ቀለብ ስዮም ባስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል ተሳታፊው ጠይቋል።
ከ6ኪሎ የጀመረው የምረጡኝ ቅስቀሳ የፍፃሜ መርሃ ግብር በፒያሳ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ስር ፓርቲው ባደረገው የመዝጊያ ንግግር ተቋጭቷል።
ባልደራስ ባደረገው የመዝጊያ ንግግር ፓርቲው ሙስሊም ጠል ነው፤የኦሮሞን ህዝብ ያገላል እንዲሁም ቢመረጥ ፐብሊክ ሰርቫንቱን ያባርራል የሚሉት ወሬዎች ቧልቶች ናቸው ብሏል።
በትግራይ ንፁሃን ወገኖቻችን ላይ በኤርትራ ሰራዊትና በሀገሬው ሰራዊት የሚደርሰውን ግፍ በፅኑ እናወግዛለን ብሏል ፓርቲው።
መንግስት በቀጣይ የሚያካሂደውን የአባይ ውሃ ሙሊት በተያዘለት መርሃ ግብር እንዲያጠናቅቅም ፓርቲው ጠይቋል።የውጭ አገራት ለሱዳን እና ለግብፅ ያደላ አካሄዳቸውን ፓርቲው እንደሚቃውም ገልጿ የተጣለው የቪዛ እገዳ ግን ተገቢ ነው ብሏል።
ባጠቃላይ የሚነዙ አሉባልታዎችን ህዝቡ ወደ ጎን በመተው ባልደራስን በመምረጥ አዲስ አበቤ ከተማውን እንዲያስተዳድር ሲል ፓርቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።
ባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ
ሰኔ 2013
ድል ለዴሞክራሲ!!