ባልደራስ ከውጪ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያየ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ የውጪ ሃገራት አምባሳደሮች ጋር በራዲሰን ብሉ ሆቴል በወቅታዊ ጉዳዬች ላይ ተወያዩ፡፡
መጪው ሃገር አቀፍ ምርጫ፣ የባለደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገወጥ እስር ፣በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች በሐይማኖታቸውን እና በማንነታቸው እየተለዩ በሚደርስባቸው ሞት እና መፈናቀል በተመለከተ ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ አሁን የታዩ ችግሮችን አስመልክቶ በባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡
የባልደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከአምባሳደሮች ጋር ያደረጉት ቆይታ ሙሉ ዘገባ በቅርቡ እናቀርባለን፡፡