ባልደራስ አጣዮን መልሶ ለመገንባት የሚውል ድጋፍ አደረገ !
ባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አጣየ ከተማን መልሶ ለመገንባት የተያዘውን መርሃ ግብር የሚያግዝ የግንባታ ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል።
ፓርቲው ለምርጫ ቅስቀሳ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የባነር መስቀያ ብረቶች እና እንጨቶችን መልሶ በመሰብሰብ ነው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገው።
ድጋፉን ለመስጠት በአጣየ ከተማ የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሂምን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አባላት ተገኝተዋል።
ባልደራስ ከዚህ ቀደም ከፖለቲካ ስራው ጎን ለጎን የተለያዮ የሰብዓዊ እርዳታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል ሃላፊዋ። ዛሬም በተመሳሳይ አጣየን መልሶ ለመገንባት ለተያዘው መርሃ ግብር ግብዓት ይሆን ዘንድ ይህንን ድጋፍ አድርገናል በለዋል። ሃላፊዋ አያይዘው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ አካላት ለዚህ በጎ ስራ እጃቸውን እንዲዘረጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ወደ ስፍራው ያቀኑት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባላት በበኩላቸው ከሃብት ንብረታቸው ተፈናቅለው ጎዳና ላይ የሚኖሩ ዜጎች ህይዎት ያሳስበናል ብለዋል። ለተፈናቃዮቹ አስቸኳይ የምግብ፣ የቁሳቁስ እና የአልባሳት ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል ።