“ባልደራስ-ለግፉዓን”
ለእስክንድር ፖለቲካ ሰብዓዊነት ነው። ሰብዓዊነት ደግሞ የዕርሱ የመጨረሻ መዳረሻ ነው።በዕውነተኛ ዴሞክራሲ ውስጥ ሰብዓዊነት ዝቅ አይልም፤ዕኩልነት አለ።ፍትህ በልኩ ይሰፍናል። ቋንቋ ከመግባቢያነት የዘለለ ሚና አይኖረውም። ባህል፡እሴት፣ታሪካዊ ቅርስ፣ዕምነት ክቡርነታቸው ፀንቶ ይቀጥላል።
እስክንድር የሰው ነገር አይሆንለትም።ከምንም በላይ ለተገፉት፣ለተራቡት፣ለተጠሙትና ለታረዙት ቀድሞ ይቆማል ።
በማንነታቸው በገዢ መንግሥታት ሰዎች በኢትዮጵያ ከዜግነት ልክ ወርደው ሲሰቃዩ እርሱ አጽናኝ፣ ተቆርቋሪና ጠበቃ ሆኖ ይመጣል። ይህ ሰው ስለምን ዕውነትን ይዘህ ትኖራለህ? በሚል ለ10 ዓመት በዕስር ቤት አሳልፏል። ዛሬም በዕርሱ ስቃይ፣ዕንግልት ፣ግርፋትና ትግል ወደ ዙፋን የመጡ ግለሰቦች ስለምን ለተገፉት ድምፅ ትሆናለህ በሚል ላለፉት 16 ወራት ቀንና ሌሊቶችን ዳግም በእስር ቤት እንዲያሳልፍ ፈርደውበታል።
እስክንድር ከወርቅ የነጣ ነው።እስክንድር ዕውነት ነው።እስክንድር የግፉዓን አንደበት ነው። ስለዚህ በአስቸኳይ ፍቱት።
https://www.facebook.com/Balderas.Ethio/videos/373740160875727/