ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ምርጫ ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (#ባልደራስ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ባልደራስን ወክለው በምርጫ ጣቢያዎች ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ ።
በመርሃግብሩ ላይ የባልደራስ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን በምርጫ 2013 አስተዋፅኦ ያደረጉ ታዛቢዎችን
ያመሰገኑ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ጊዜያትም በተጠናከረ መልኩ ከባልደራስ ፓርቲ ጋር በአጋርነት አብረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
የምስጋና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው አባላት እና ደጋፊዎችም ባልደራስን በሚችሉት ነገር ሁሉ እንደሚያገለግሉ ገልፀዋል።
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ!