ለሚዲያዎች ሁሉ !
ጉዳዩ ፦ ከሃገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ የፕሬስ ኮንፈረንስ ጥሪን ይመለከታል !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ በሆነ መንገድ እውቅና አግኝቶ የመጪው ሃገራዊ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲ ሆኖ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ መርሃ ግብር መሰረት እጩዎቹን በማስመዝገብ በኩልና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገራችን ህዝብ ገለፃ ለማድረግ አቅዷል ።
በመሆኑም መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ስድስት ኪሎ ከመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን 500 ሜትር ያህል ከፍ ብሎ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤታችን ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።
በዚህ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ከምርጫው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለህዝቡ እንድታቀርቡልን እንጠይቃለን።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
አዲስ አባባ
መጋቢት 1, 2013 ዓ.ም
መጋቢት 1, 2013 ዓ.ም