የግፍ እስረኛው አቶ ናትናኤል ያለምዘድ ላይ 12 ቀናት ተሰጠባቸው
በግፍ እስር ላይ ይሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ለዛሬ ፍ/ቤት እንደሚቀርቡ መዘገባችን ይታወሳል። በቀጥሯቸው መሰረትም ዛሬ ሰኔ 5/2016 ዓ.ም በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።
ችሎቱ ከትላንት በስቲያ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜና የእስረኞች ጠብቆች ያቀረቡትን መቃወሚያ መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር የተሰየመው። በዚህም መሰረት ፍ/ቤቱ በእነ አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ላይ ተጨማሪ 12 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዶባቸዋል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በስራ አፈፃሚ አባሉ አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ፣ በሚዲያ ክፍል ጋዜጠኛው ወንድምነው አድማስ እንዲሁም በሌሎች የግፍ እስረኞች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን በደል እና ኢ-ሠብአዊ ድርጊት አጥብቆ ያወግዛል። በአስቸኳይ እንዲፈቱም ያሳስባል።
የግፍ እስረኞች ይፈቱ!