የህግ የበላይነት እና የፍትህ አካላት ሚና ምን መሆን አለበት?
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ስለህግ የበላይነት እና የፍትህ አካላት ሚና በአማራጭ መፍትሔነት በምርጫ ማኒፌስቶ (መጋቢት፣ 2013 ዓም) በግልፅ እንዳስቀመጠው “በኢትዮጵያ የሚኖረው የፖለቲካ ሥረዓት የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ይሆናል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ ወይም መንግስታዊ አካል ለህግ የበላይነት ተገዢ ይሆናል፡፡ መንግስት የሚመራበት ህግ ግልፅ የሆነ፣ አስቀድሞ በአዋጅ የወጣና የግለሰቦችን መሰረታዊ ሰበዓዊ መብት የሚጠብቅና ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ማንኛውም ግለሰብ ከህግ አግባብ ውጪ መብቱን፣ ነፃነቱን፣ ንብረቱን እና ጥቅሞች እንዳይነኩ የህግ ጥብቃና ዋስትና ያገኛል፡፡ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ነፃ፣ ገለልተኛ እና ተደራሽነት ያላቸው የፍትህ አካላት በየደረጃው ይቋቋማሉ፡፡ በህዝብ ተሳትፎና ነፃ ምርጫ የሚፀድቀው ህገ መንግስት የሁሉም ህጎችና መንግስታዊ ውሳኔዎች የበላይ ሆኖ ያገለግላል፡፡”
እኛ ባልደራሶች የህግ የበላይነት የማይገረሰስበት እንዲሁም ፍትህ የሰፈነባትን ታላቅ የሠለጠነች አገር እንድትኖረን ዘውትር መትጋት ግዴታችን ነው!!!!
* * * * *
ኢንጂነር ዓለማየሁ ንጋቱ
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ምርጫ ክልል 19 የባልደራስ የፓርላማ ዕጩ ተወዳዳሪ
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ