እንኳን ለ80ኛው ዓመት የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል አደረሠን !
ክብር ለአርበኞቻችን !!
ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈቷ 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ደርጅታ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙሶሎኒ ትዕዛዝ ኢትዮጵያን ከሦስት አቅጣጫዎች ወረረች፡፡ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ የዘመተው የጣልያኑ ጦር አዛዥ ጄኔራል ባዶሊዩ አዲስ አበባ ገብቶ በታላቁ ቤተ መንግሥት የጣሊያንን ባንዲራ ሰቀለ። ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር በፅናት ተዋጋች ፡፡ በጀግኖች አርበኞች ብርታትና መስዋዕትነት ተሰቅሎ የነበረው የጣሊያን ባንዲራ ከ5 ዓመታት በኋላ ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ/ም ወርዶ በምትኩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በክብር ተሰቀለ፡፡
በዛሬው እለት ሚያዚያ 27 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አርበኞች የድል በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ፤ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራርና አባላት ፤ የጀግኖች አርበኞች የመታሰቢያ የድል ሐዉልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። እለቱን በማስመልከት የባልደራስ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ እንዲሁም የባልደራስ ዕጩ የህዝብ ተወካዮች ም/ር ቤት ተወዳዳሪዎች በቦታው ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ !!!