አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ በአገዛዙ ሀይሎች ታፈነ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው አቶ ናትኤል ያለምዘውድ ዛሬ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቱ በአገዛዙ ሀይሎች ታፍኖ መወሰዱን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል፡፡
የግፍ እስረኛው ናትኤል ያለምዘውድ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ እስር ላይ ይገኛል።
የግፍ እስረኞች ይፈቱ!
ድል ለዲሞክራሲ!