ባልደራስ ጋዜጣ(BALDERAS NEWSPAPER)
ዘር ማጥፋት ወይስ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል?
እስክንድር ነጋ፣ የህሊና እስረኛ፤ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፣ አዲስ አበባከሁሉ አስቀድሞ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሀጫሉ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ስለተከሰተው ሁኔታ ያወጣው ሪፖርት ምሥጋና ይገባዋል፡፡ የሚንቀሳቀስበትን አውድ ግምት ውስጥ እናስገባለት፡፡ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ በጐ እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗ የሚካድ ባይሆንም፣ በሰብዓዊ መብት አክባሪነታቸው ከሚወደሱ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ግን አልታደለችም፡፡ በፍጥነት የሚበቅልና የሚለመልም […]
ውስጠ ወይራው ያለመለወጥ ‹ለውጥ› (፪)
በክፍል አንድ መጣጥፌ ‹ለውጥ› እየተባለ የሚወራው ሀሰት መሆኑን አብራርቻለሁ፡፡ ‹ለውጥ› ተብየው ውስጠ ወይራ እንደሆነ እና ‹የለውጡ› መሪ ነኝ ባዩ አብይ አሕመድ ነብረው የወጡት ወያኔ የጣለውን እንቁላል እንደሆነ አብራርቻለሁ፡፡ በ‹ለውጥ› ሽፋን ‹ለውጥን› የመከላከል ቁልቁለቱ አያሌ ርዕዮተ ዓለማዊ፣ ሕገ መንግሥታዊ፣ ተቋማዊ እና ሥርዓታዊ መገለጫዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ሦስት መገለጫዎችን ቀንጭቤ እገልፃለሁ፡፡ አንደኛው የአዳፍኔነትና የአስቀጣይነት መንታ ስለት ሲሆን […]
የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ጥቅምና ጉዳት ጉዳይ ሙያዊ ቅኝት (ነብዩ ውብሸት)
አፄ ምኒሊክና የመጀመሪያው የስልክ ግንኙነት ኢትዮጵያ፣በ1886ዓ.ም፣በታላቁ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት፣ የመጀመሪያውን የ477 ኪ.ሜ የስልክ መሥመር ዘርግታ፣“ጤና ይስጥልኝ ዐዲስ!! ጤና ይስጥልኝ ሐረር!!” ካስባለች፣126 ዓመታት ተቆጠሩ። አፄ ምኒሊክ፣ሀገሪቷን ያስተዳድሩ በነበሩበት ዘመን ያስገቧቸውን፣ዘመናዊ አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ብዛት ስናይ፣አፄ ምኒሊክ፣“የሥልጣኔ ማግኔት ነበሩ!!” ለማለት እንችላለን። አፄ ኃይለሥላሴና የቴሌኮሙኒኬሽን እድገት ኹኔታ የቴሌፎን ቴክኖሎጂ ወደ ኢትጵያ የገባው፣በ1886 ዓ.ም በምኒልክ […]
“ገበታ ለሀገር” – ከዶሮና ዓሳ ወግ አንጻር(ከማለፊያ ደርሰህ)
ዶሮና ዓሳ የቀረበ ገበታ አይተው ወግ ይጀምራሉ:: በገበታው ላይ የቀረበው ምግብ የዕንቁላል ጥብስና ዓሳ ነው:: ዶሮው “ይህ ገበታ ጣፋጭ ሆኖ ትላልቅ መሳፍንትና መኳንንት ተደስተው እንዲመገቡ ለማድረግ የእኔ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው:: ምክንያቱም እንቁላሉን የጣለችው ሚስቴ ዶሮ ነች፤ እንቁላሉ የሁለታችንም ዶሮዎች አበርክቶ ነው” ብሎ ተኩራራ::ዓሳውም ተደንቆ “እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳሉ” ብሎ ተረተና “ሰማህ ዶሮ፣ […]
ሙሉ መጽሔቱን ለማውረድ/ Download