ለባልደራስ ክስ ምርጫ ቦርድ ነገ በፍርድ ቤት መልስ ያቀርባል !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ምርጫ 2013 ላይ የተሠሩ ሕገ ወጥ ተግባራትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅሬታዎችን ቢያቀርብም ከሕግ አግባብ ውጭ በማን አለብኝነት ውድቅ ተደርገውበታል። በመሆኑም ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶ በምርጫ ቦርድ ላይ ሕጋዊ ክስ መስርቷል።
ፓርቲው ለመሰረተው ሕጋዊ ክስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነገ ሀምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ መልስ ይሰጣል። ክሱ በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች እና በ21 የምርጫ ክልሎች ላይ የተፈፀመን ሕገ ወጥነት የሚመለከት ሲሆን በፌዴራል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ ለይ የተፈፀሙትን ሁሉ ይዳስሳል።